የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ዜና መዋዕል 3:1-10

1 ዜና መዋዕል 3:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በኬ​ብ​ሮን ለዳ​ዊት የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። በኵሩ አም​ኖን ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዶለ​ህያ ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቢ​ግያ፥ ሦስ​ተ​ኛው አቤ​ሴ​ሎም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከተ​ል​ማይ ልጅ ከመ​ዓካ፥ አራ​ተ​ኛው አዶ​ን​ያስ ከአ​ጊት፥ አም​ስ​ተ​ኛው ሰፋ​ጥ​ያስ ከአ​ቢ​ጣል፥ ስድ​ስ​ተ​ኛው ይት​ር​ኃም ከሚ​ስቱ ከዔ​ግላ። እነ​ዚህ ስድ​ስቱ በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በዚ​ያም ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። እነ​ዚህ ደግሞ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ ከዓ​ሚል ልጅ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥ አራት፤ ኢያ​ቤ​ሔር፥ ኤል​ሳማ፥ ኤሊ​ፋ​ላት፥ ናጌል፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ ኤል​ሳማ፥ ኤሊዳ፥ ኤል​ፋ​ሌጥ፥ ዘጠኝ። እነ​ዚህ ሁሉ ከቁ​ባ​ቶቹ ልጆች በቀር የዳ​ዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕ​ማ​ርም እኅ​ታ​ቸው ነበ​ረች። የሰ​ሎ​ሞ​ንም ልጅ ሮብ​ዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥

1 ዜና መዋዕል 3:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የበኵር ልጁ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም፣ ሁለተኛው ዳንኤል፣ ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ፣ ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣ አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣ ዐምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያ፣ ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም። እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር። ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው። ኢያቤሐር፣ ኤሊሳማ፣ ኤሊፋላት፣ ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣ ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላሉ፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ። ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው። የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ የሮብዓም ልጅ አብያ፣ የአብያ ልጅ አሳ፣ የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣

1 ዜና መዋዕል 3:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦ በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥ ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤ እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት በኬብሮን ሲሆን ዳዊት መኖሪያውን በዚያ አድርጎ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ወቅት ነው። ዳዊት መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ ሦስት ዓመት ገዛ፤ በዚያም ብዙ ወንዶች ልጆችን ወለደ። የዓሚኤል ልጅ ቤርሳቤህ ሺምዓ፥ ሾባብ፥ ናታንና ሰሎሞን ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት። ሌሎች ዘጠኝ ወንዶች ልጆችም ነበሩት፤ እነርሱም ይብሐር፥ ኤሊሹዓ፥ ኤሊፋሌጥ፥ ኖጋህ፥ ኔፌግ፥ ያፊዓ፥ ኤሊሻማዕ፥ ኤሊያዳዕና ኤሊፌሌጥ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ ዳዊት ከቊባቶቹ የወለዳቸው ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ትዕማር ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅም ነበረችው። የንጉሥ ሰሎሞን የትውልድ ሐረግ ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፥ ሰሎሞን፥ ሮብዓም፥ አቢያ፥ አሳ፥ ኢዮሣፍጥ፥

1 ዜና መዋዕል 3:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በኬብሮንም ለዳዊት የተለወዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኩሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዳንኤል ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፤ ሦስተኛው አቤሴሎም የመዓካ ልጅ እርሷም የጌሹር ንጉሥ የተልማይ ልጅ ነበረች፥ አራተኛው አዶንያስ የአጊት ልጅ፤ አምስተኛው ሰፋጥያስ ከአቢጣል፥ ስድስተኛው ይትረኃም ከሚስቱ ከዔግላ፤ ስድስቱ በኬብሮን ተወለዱለት፤ በዚያም ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ አራት ልጆች እነርሱም ሳምዓ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፤ ከዚያም በኋላ ኢያቤሐር፥ ኤሊሱዔ፥ ኤሊፋላት፥ ኖጋ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት ዘጠኝ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ከቁባቶች ልጆች በቀር የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕማርም እኅታቸው ነበረች። የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮሣፍጥ፥