የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 25

25
የቤተ መቅደስ መዘምራን
1ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ። 2ከአሳፍ ልጆች ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ እጅ በታች ነበሩ። 3ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም እጅ በታች ነበሩ። 4ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤል፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር፥ ዩሽብቃሻ፥ መሎቲ ሆቲር፥ መሐዝዮት፤ 5እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራዕይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው። 6እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም ይዘምሩ ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ ከአባታቸው እጅ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ። 7የብልሃተኞቹም ቍጥር እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሚያውቁ ከወንድሞቻቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ። 8ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።
9የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎልዶያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹን አሥራ ሁለት ነበሩ፤ 10ሦስተኛው ለዘኩር ለልጆቹም ለወንድሞቹም 11ለዐሥራ ሁለቱ፤ አራተኛው ለይጽሪ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤ 12አምስተኛው ለነታኒያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 13ስድስተኛው ለቡቅያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐአሥራ ሁለቱ፤ 14ሰባተኛው ለይሽርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 15ስምንተኛው ለየሻያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ዐአሥራ ሁለቱ፤ 16ዘጠነኛው ለመታንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 17ዐሥረኛው ለሰሜኢ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 18ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 19ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሽብያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤ 20ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 21ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 22ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 23ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለፀሥራ ሁለቱ፤ 24ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤ 25ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐአሥራ ሁለቱ፤ 26ዐሥራ ዘጠነኛው ለመሎቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 27ሃያኛው ለኤልያታ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 28ሃያ አንደኛው ለሆቲር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአዐሥራ ሁለቱ፤ 29ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 30ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ፤ 31ሃያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ ወጣ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ