አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 24
24
የካህናት አመዳደብ
1የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ። 2ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆኑ። 3ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዐርት ከፍሎ መደባቸው። 4የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች አሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ። 5ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና የእግዚአብሔር አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ። 6ከሌዊያውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ።
7መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ፥ 8ሦስተኛው ለካሪም፥ አራተኛው ለሥዖሪም፥ 9አምስተኛው ለመልክያ፥ ስድስተኛው ለሚያሚን፥ 10ሰባተኛው ለአቆስ፥ ስምንተኛው ለአብያ፥ 11ዘጠነኛው ለኢያሱ፥ ዐሥረኛው ለሴኬንያ፥ 12ዐሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂን፥ 13ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፥ ዐሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፥ 14ዐሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፥ ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፥ 15ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፥ ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፥ 16ዐሥራ ዘጠኝኛው ለፈታያ፥ ሃያኛው ለኤዜቄል፥ 17ሃያ አንደኛው ለያኪን፥ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፥ 18ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፥ ሃያ አራተኛው ለመዓዝያ። 19የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዐት ይህ ነበረ።
የተቀሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር
20ከቀሩትም የሌዊ ልጆች፤ ከእንበረም ልጆች ሱባኤል፤ ከሱባኤል ልጆች ዬሕድያ፤ 21ከዓረብያ ልጆች አለቃው ይሺያ፤ 22ከይስዓራውያን ሰሎሚት፤ ከሰሎሚት ልጆች ያሐት፤ 23ከኬብሮንም ልጆች አለቃው ይሪያ፥ ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው የሕዚኤል፥ አራተኛ ይቀምዓም፤ 24የዑዝኤል ልጅ ሚካ፤ የሚካ ልጅ ሻሚር፤ 25የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ልጆች ዘካሪያስ፤ 26የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ፤ የያዝያ ልጅ በኖ፤ 27የሜራሪ ልጆች ከያዝያ በኖ፥ ሾሃም፥ ዘኩር፥ ዔብሪ፤ 28ከሞሖሊ አልዓዛር፥ እርሱም ልጆች አልነበሩትም፤ 29ከቂስ፥ የቂስ ልጅ ይረሕምኤል፤ 30የሙሲም ልጆች ሞሖሊ፥ ዔደር፥ ኢያሪሙት። እነዚህም እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ። 31እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላቁም እንደ ታናሹ፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 24: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ