የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ጥበብ 17

17
በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ፍር​ሀት በሌ​ሊት እንደ ወደ​ቀ​ች​ባ​ቸው
1ፍር​ድህ ታላቅ ነው፥ ለመ​ና​ገ​ርም ድንቅ ነው። ስለ​ዚ​ህም የፈ​ጣሪ ትም​ህ​ርት የሌ​ላ​ቸው ሰው​ነ​ቶች ሳቱ። 2ኃጥ​ኣን ቅዱስ ሕዝ​ብን በያዙ ጊዜ፥ በተ​በ​ረ​ታ​ቱ​ባ​ቸ​ውም ጊዜ፥ ኀያ​ላ​ንም በረ​ዥም የሌ​ሊት ጨለማ በታ​ሰሩ ጊዜ ያን​ጊዜ በቤ​ታ​ቸው ጣራ ስር ተጋዙ። ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ማ​ዊው አገ​ል​ግ​ሎት ሥር​ዐ​ትም ሸሸ​ተው ተገኙ። 3የበ​ደ​ሉ​ት​ንም ዐስ​በው በው​ስጡ ብር​ሃን በሌ​ለ​በት ቤት ውስጥ ከዝ​ን​ጋዔ መጋ​ረጃ በታች ተሰ​ወሩ፥ እጅ​ግም እየ​ተ​ደ​ነቁ በድ​ን​ጋጤ ቀለጡ፥ በም​ት​ሀ​ትም ታወኩ። 4የያ​ዛ​ቸው አመ​ን​ዝራ#ግሪኩ “ያሉ​በት አዳ​ራሽ” ይላል። ከድ​ን​ጋጤ ይጠ​ብ​ቃ​ቸው ዘንድ አል​ቻ​ለም፥ ነገሩ ስቅ​ጥጥ የሚ​ያ​ደ​ርግ የታ​ላቅ ቃል ድም​ፅም ያው​ካ​ቸው ጀመር። የክፉ ምት​ሀት መል​ክም ፊቱ ያዘ​ነ​ውን ሁሉ አጠፋ። 5የእ​ሳ​ቱም ብር​ሃን አን​ዲት ሰዓት እንኳ ያበራ ዘንድ አል​ቻ​ለም፥ የብ​ሩ​ሃን ከዋ​ክ​ብት ብር​ሃ​ንም ለዚ​ያች ለም​ታ​ስ​ፈ​ራዋ ሌሊት ጨለማ ያበራ ዘንድ አል​ቻ​ለም። 6ነገር ግን ከዚህ ከሚ​ታ​የው መልክ ይልቅ ግር​ማው ፍጹም የሆነ፥ ከማ​ይ​ታ​ዩ​ትም መል​ኮች ይልቅ የከፋ ብቸኛ እሳት ድን​ገት ታያ​ቸው። 7በሚ​ሳ​ደ​ቡት ላይ የት​ዕ​ቢት ዘለፋ ሊሆ​ን​ባ​ቸው የስ​ን​ፍና ድካም የሆነ የሟ​ርት ሥራን ከወ​ር​ቅና ከብር አደ​ረጉ። 8ከታ​መ​መች ሰው​ነት ሁከ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን ያስ​ወ​ግዱ ዘንድ ተስፋ የሰጡ እነ​ዚ​ህን ፍር​ሀት አሳ​መ​ማ​ቸው፥ ለሣ​ቅም የተ​ገቡ ሆኑ።
9የሚ​ያ​ው​ከው ነገር ምንም ባያ​ስ​ፈ​ራ​ቸው የሚ​በ​ርር ተሓ​ዋሲ እን​ቅ​ስ​ቃ​ሴና የእ​ባ​ቦች ጩኸት አባ​ረ​ራ​ቸው። አስ​ደ​ን​ግ​ጦም አሸ​ሻ​ቸው። ከሁሉ አቅ​ጣጫ የሚ​ሸሽ ነፋ​ስ​ንም ማየት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም። 10የክፉ ሰው ሥራው የሚ​ያ​ስ​መ​ሰ​ክ​ር​በ​ትና የሚ​ያ​ስ​ፈ​ር​ድ​በት ዐመፅ ነው፥ ሁል​ጊ​ዜም እየ​ታ​ወ​ቀ​ውና ዕው​ቀት ባለው ሕሊና እየ​ተ​መ​ለ​ከተ ክፉና ጠማማ ሥራን ይቀ​በ​ላል፥ ይሠ​ራ​ልም። 11ፍር​ሀት ምንም አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን የፍ​ርድ ጥር​ጥ​ርን በሕ​ሊና ያሳ​ድ​ራል። 12ጥቂት ወይም ጐደሎ የል​ቡና ጥር​ጥር ብት​ኖ​ርም ባለ​ማ​ወቅ ነው፥ በስ​ን​ፍ​ናም ነው፥ ለፍ​ር​ድም መን​ገድ የም​ት​ሰጥ ናት ተብላ ትታ​ሰ​ባ​ለች። 13በእ​ው​ነት ሊታ​ገ​ሡ​አት ከማ​ይ​ቻል ከሲ​ኦል ጕድ​ጓድ የወ​ጣች ያች ሊታ​ገ​ሡ​አት የማ​ይ​ቻል ሌሊት እነ​ር​ሱን በሸ​ፈ​ነ​ቻ​ቸው ጊዜ ያችን ቀን ተኝ​ተው ነበር። 14የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጡ አጋ​ን​ንት አስ​ደ​ን​ግ​ጠ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና፥ ምት​ሀ​ትን በማ​ሳ​የት የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው አሉ፥ የሰ​ው​ነ​ት​ንም ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ክም አለ፥ ያል​ጠ​በ​ቁ​ትና ያል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ሩት ፍር​ሀ​ትና ድን​ጋ​ጤም ድን​ገት ደረ​ሰ​ባ​ቸው። 15በዚ​ያም ያለው ማን​ኛ​ውም ሁሉ እን​ዲህ ነው፥ የወ​ደ​ቀም ቢሆን፥ በእ​ግር ብረት ወይም ያለ እግር ብረት ታስሮ በእ​ስር ቤት የሚ​ጠ​በ​ቅም ቢሆን፥ 16አራ​ሽም ቢሆን፥ እረ​ኛም ቢሆን፥ በም​ድረ በዳ ተቀ​ምጦ ምድ​ርን በማ​ረስ የሚ​ደ​ክም ምን​ደ​ኛም ቢሆን፦ ያገ​ኘ​ች​ውን ያችን አስ​ጨ​ናቂ መከራ ታግ​ሦ​አ​ልና።
17ማኅ​በ​ራ​ቸው በአ​ን​ዲት የጨ​ለማ እግር ብረት ታስ​ሯ​ልና ያገ​ኛ​ቸው ምት​ሀት እን​ዲህ ነው፥ የሚ​ያ​ፏጭ ምት​ሀት፥ ወይም ጭፍቅ ካሉና ከሚ​ያ​ስ​ጠ​ልሉ ከዛ​ፎች የተ​ነሣ ድምፁ ያማረ የቅ​ር​ን​ጫ​ፎች ቃል ወይም ዜማ​ቸው ያማረ የወ​ፎች ድምፅ፥ 18ወይም በኀ​ይል የሚ​ሄድ የውኃ ሿሿቴ ድምፅ፥ ወይም በማ​ስ​ፈ​ራ​ራት የሚ​ገ​ለ​ባ​በጡ የዋ​ሻ​ዎች ድምፅ፥ ወይም የሚ​ሮ​ጡና ሩጫ​ቸው የማ​ይ​ታይ የእ​ን​ስ​ሳት ሩጫ፥ ወይም በሚ​ያ​ስ​ፈራ ቃል የሚ​ጮኹ የአ​ው​ሬ​ዎች ጩኸት፥ ወይም ከአ​ዕ​ዋ​ፍና ከአ​ራ​ዊት ድምፅ የተ​ነሣ እርስ በር​ሳ​ቸው ድም​ፅን ለዋ​ው​ጠው የሚ​መ​ልሱ የሚ​ያ​ስ​ፈሩ የተ​ራ​ራ​ዎች ድምፅ ነው። አስ​ደ​ን​ግ​ጦም ያጠ​ፋ​ቸው መከራ እን​ዲህ ነው። 19ዓለሙ ሁሉ በሚ​ያ​በራ ብር​ሃን ይበራ ነበ​ርና፥ ያለ​ማ​ቋ​ረ​ጥና ያለ​መ​ከ​ል​ከ​ልም ሥራ​ውን ይፈ​ጽም ነበ​ርና። 20እነ​ዚ​ህን ግን ብቻ​ቸ​ውን ይወ​ስ​ዳ​ቸው ዘንድ ያለው የጨ​ለማ ምሳሌ የሆ​ነው የሌ​ሊት ክብ​ደት ሰወ​ራ​ቸው፥ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም ለራ​ሳ​ቸው ከጨ​ለማ የጸኑ ናቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ