ክርስቶስም እና ኀጢአተኞች ስንሆን ስለ ኀጢአታችን ይሞት ዘንድ ዘመኑ ሲደርስ መጣ። ስለ ክፉዎች በጭንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚደፍር አይገኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚጨክን የሚገኝ እንዳለ እንጃ። እግዚአብሔር ምን ያህል እንደ ወደደን እነሆ፥ እዩ፤ እና ኀጢአተኞች ስንሆን ክርስቶስ ስለ እና ሞተ። እንግዲህ በደሙ ዛሬ ከጸደቅን ከሚመጣው መከራ በእርሱ እንድናለን። እና የእግዚአብሔር ጠላቶቹ ስንሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታረቀን በኋላም በልጁ ሕይወት እንዴት የበለጠ ያድነን! በዚህ ብቻ አይደለም፤ በእርሱ ይቅርታውን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም በእግዚአብሔር ዘንድ እንመካለን እንጂ። ስለዚህም በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ፤ እንደዚሁም ሁሉ ኀጢአትን ስለ አደረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ። ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢአት ምን እንደ ሆነች ሳትታወቅ በዓለም ውስጥ ነበረች፤ ነገር ግን የኦሪት ሕግ ገና ስላልመጣ ኀጢአት ተብላ አትቈጠርም ነበር። ነገር ግን በአዳም ኀጢአት ምክንያት ከአዳም እስከ ሙሴ የበደሉትንም ያልበደሉትንም ሞት ገዛቸው፤ ሁሉ በአዳም አምሳል ተፈጥሮአልና፥ አዳምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና። ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋው በበደላችን መጠን የሆነብን አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ከሞቱ፥ እንግዲህ በእግዚአብሔር ጸጋ፥ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በሰጠን ሀብቱ ሕይወት በብዙዎች ላይ እንዴት እጅግ ይበዛ ይሆን? የእግዚአብሔር ጸጋው በአንዱ ሰው ኀጢአት መጠን የሆነብን አይደለም፤ የኀጢአት ፍርድ ከአንድ ሰው ወጥታ ሁሉ ከተቀጣባት፥ ጸጋው ከበደላችን እንደ ምን ያነጻን ይሆን? የዘለዓለምንስ ሕይወት እንዴት ይሰጠን ይሆን? የአንዱ ሰው ኀጢአት ሞትን ካነገሠችው በአንድ ሰው በደልም ሞት ከገዛን፥ የአንዱ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ የጸጋው ብዛትና የጽድቁ ስጦታ እንዴት እጅግ ያጸድቀን ይሆን? የዘለዓለም ሕይወትንስ እንዴት ያበዛልን ይሆን? እንግዲህ በአንዱ ሰው በደል ዓለም ሁሉ እንደ ተፈረደበት፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ ሰው ጽድቅ ሰው ሁሉ ይጸድቃል። በአንድ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንድ ሰው መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። ኦሪትስ ኀጢአትን ታበዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢአትም ከበዛች ዘንድ የእግዚአብሔር ጸጋ በዛች። ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች።
ወደ ሮሜ ሰዎች 5 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ሮሜ ሰዎች 5
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos