የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሮሜ 5:6-21

ሮሜ 5:6-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ገና ደካሞች ሆነን ሳለ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞተ። በጻድቅ ምትክ ሆኖ የሚሞት ሰው ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም በደግ ሰው ምትክ ለመሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል። እንግዲህ የጸደቅነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሆነ ይበልጡንም ከእግዚአብሔር ቊጣ የምንድነው በእርሱ አማካይነት ነው። እኛ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ሳለ በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል፤ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን በኋላ በልጁ ሕይወት አማካይነት ይበልጡን እንድናለን። ይህም ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነትም በእግዚአብሔር እንመካለን። በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአት ምክንያትም ሞት መጣ፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ኃጢአትን ስለ ሠራ ሞት በሰው ሁሉ ላይ መጣ፤ የሙሴ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ነበር፤ ይሁን እንጂ ሕግ በሌለበት ኃጢአት ራሱ እንደ ኃጢአት አይቈጠርም ነበር። ሆኖም እንደ አዳም ሕግን በመተላለፍ ኃጢአት ባልሠሩት ላይ እንኳ ሳይቀር ሞት ከአዳም አንሥቶ እስከ ሙሴ ድረስ በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን አገኘ። ይህ አዳም ወደፊት ለሚመጣው ክርስቶስ ምሳሌ ነበረ። ነገር ግን የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታው እንደ ሰው ኃጢአት አይደለም፤ በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ብዙዎች እንደ ሞቱ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት የተገኘው የጸጋ ስጦታ ለብዙዎች ተትረፍርፎ ተሰጥቶአል። እንዲሁም የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታው ያመጣው ጸጋ ውጤት የአንድ ሰው ኃጢአት እንዳመጣው ውጤት አይደለም። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ፍርድ ቅጣትን አመጣ፤ በብዙ ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ነጻ ስጦታ ጽድቅን አመጣ። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ሞት በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን ካገኘ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና ነጻ ስጦታ ተቀብለው የጸደቁ ሁሉ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በድል አድራጊነት በሕይወት ይኖራሉ። እንግዲህ የአንዱ የአዳም ኃጢአት የቅጣትን ፍርድ በሰው ሁሉ ላይ እንዳመጣ እንዲሁም የአንዱ የክርስቶስ የጽድቅ ሥራ ብዙዎችን ከቅጣት ነጻ አድርጎ ሕይወትን ይሰጣል። በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁም በክርስቶስ መታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ይጸድቃሉ። ኃጢአት ይበዛ ዘንድ ሕግ መጣ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛ መጠን የእግዚአብሔር ጸጋ በይበልጥ በዛ። ይህም የሆነው በሞት ምክንያት ኃጢአት እንደ ነገሠ ሁሉ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን በመስጠት ይነግሣል።

ሮሜ 5:6-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ገና ደካሞች ሳለን፣ ልክ ጊዜው ሲደርስ፣ ክርስቶስ ስለ ኀጢአተኞች ሞቷልና። ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል። አሁን በደሙ ከጸደቅን፣ ይልቁንማ በርሱ በኩል ከእግዚአብሔር ቍጣ እንዴት አንድንም! የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከርሱ ጋራ ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን። ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቷል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኀጢአት በዓለም ላይ ነበር፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኀጢአት አይቈጠርም። ይሁን እንጂ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ባሉት፣ እንደ አዳም ሕግን በመጣስ ኀጢአት ባልሠሩት ላይ እንኳ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው አምሳሉ ነበረ። ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን አይደለም፤ በአንድ ሰው መተላለፍ ብዙዎቹ ከሞቱ፣ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው፣ ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የመጣው ስጦታ ለብዙዎች እንዴት አብልጦ ይትረፈረፍ! ደግሞም የእግዚአብሔር ስጦታ እንደ አንዱ ሰው የኀጢአት ውጤት አይደለም፤ ምክንያቱም ፍርዱ የአንድን ሰው ኀጢአት ተከትሎ ኵነኔን አመጣ፤ ስጦታው ግን አያሌ መተላለፍን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ። በአንድ ሰው መተላለፍ ምክንያት ሞት በዚህ ሰው በኩል የነገሠ ከሆነ፣ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅ ስጦታ የተቀበሉት፣ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዴት አብልጠው በሕይወት አይነግሡ! ከእንግዲህ በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ኵነኔ በሁሉ ሰው ላይ እንደ መጣ፣ እንዲሁም በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ጽድቅ ተገኘ። በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። ሕግ በመምጣቱ መተላለፍ በዛ፤ ነገር ግን ኀጢአት በበዛበት ጸጋ አብልጦ የተትረፈረፈ ሆነ፤ ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደ ነገሠ ሁሉ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ እንዲነግሥ ነው።

ሮሜ 5:6-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ክር​ስ​ቶ​ስም እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ይሞት ዘንድ ዘመኑ ሲደ​ርስ መጣ። ስለ ክፉ​ዎች በጭ​ንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚ​ደ​ፍር አይ​ገ​ኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚ​ጨ​ክን የሚ​ገኝ እን​ዳለ እንጃ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ያህል እንደ ወደ​ደን እነሆ፥ እዩ፤ እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ክር​ስ​ቶስ ስለ እና ሞተ። እን​ግ​ዲህ በደሙ ዛሬ ከጸ​ደ​ቅን ከሚ​መ​ጣው መከራ በእ​ርሱ እን​ድ​ና​ለን። እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቹ ስን​ሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታ​ረ​ቀን በኋ​ላም በልጁ ሕይ​ወት እን​ዴት የበ​ለጠ ያድ​ነን! በዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ርሱ ይቅ​ር​ታ​ውን ባገ​ኘ​ን​በት በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​መ​ካ​ለን እንጂ። ስለ​ዚ​ህም በአ​ንድ ሰው በደል ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለ​ዚ​ችም ኀጢ​አት ሞት ገባ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ ኀጢ​አ​ትን ስለ አደ​ረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ። ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢ​አት ምን እንደ ሆነች ሳት​ታ​ወቅ በዓ​ለም ውስጥ ነበ​ረች፤ ነገር ግን የኦ​ሪት ሕግ ገና ስላ​ል​መጣ ኀጢ​አት ተብላ አት​ቈ​ጠ​ርም ነበር። ነገር ግን በአ​ዳም ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ከአ​ዳም እስከ ሙሴ የበ​ደ​ሉ​ት​ንም ያል​በ​ደ​ሉ​ት​ንም ሞት ገዛ​ቸው፤ ሁሉ በአ​ዳም አም​ሳል ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፥ አዳ​ምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእ​ርሱ አም​ሳሉ ነውና። ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በበ​ደ​ላ​ችን መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ በአ​ንድ ሰው በደል ብዙ​ዎች ከሞቱ፥ እን​ግ​ዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ፥ በአ​ንዱ ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቤዛ​ነት በሰ​ጠን ሀብቱ ሕይ​ወት በብ​ዙ​ዎች ላይ እን​ዴት እጅግ ይበዛ ይሆን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ የኀ​ጢ​አት ፍርድ ከአ​ንድ ሰው ወጥታ ሁሉ ከተ​ቀ​ጣ​ባት፥ ጸጋው ከበ​ደ​ላ​ችን እንደ ምን ያነ​ጻን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንስ ሕይ​ወት እን​ዴት ይሰ​ጠን ይሆን? የአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት ሞትን ካነ​ገ​ሠ​ችው በአ​ንድ ሰው በደ​ልም ሞት ከገ​ዛን፥ የአ​ንዱ ሰው የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጸ​ጋው ብዛ​ትና የጽ​ድቁ ስጦታ እን​ዴት እጅግ ያጸ​ድ​ቀን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ት​ንስ እን​ዴት ያበ​ዛ​ልን ይሆን? እን​ግ​ዲህ በአ​ንዱ ሰው በደል ዓለም ሁሉ እንደ ተፈ​ረ​ደ​በት፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንዱ ሰው ጽድቅ ሰው ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል። በአ​ንድ ሰው አለ​መ​ታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ኀጢ​አ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንድ ሰው መታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ። ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢ​አ​ትም ከበ​ዛች ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዛች። ኀጢ​አ​ትም ሞትን እንደ አነ​ገ​ሠ​ችው እን​ዲሁ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ጽድ​ቅን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ታነ​ግ​ሠ​ዋ​ለች።

ሮሜ 5:6-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ገና ደካሞች ሳለን፣ ልክ ጊዜው ሲደርስ፣ ክርስቶስ ስለ ኀጢአተኞች ሞቷልና። ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል። አሁን በደሙ ከጸደቅን፣ ይልቁንማ በርሱ በኩል ከእግዚአብሔር ቍጣ እንዴት አንድንም! የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከርሱ ጋራ ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን። ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቷል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኀጢአት በዓለም ላይ ነበር፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኀጢአት አይቈጠርም። ይሁን እንጂ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ባሉት፣ እንደ አዳም ሕግን በመጣስ ኀጢአት ባልሠሩት ላይ እንኳ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው አምሳሉ ነበረ። ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን አይደለም፤ በአንድ ሰው መተላለፍ ብዙዎቹ ከሞቱ፣ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው፣ ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የመጣው ስጦታ ለብዙዎች እንዴት አብልጦ ይትረፈረፍ! ደግሞም የእግዚአብሔር ስጦታ እንደ አንዱ ሰው የኀጢአት ውጤት አይደለም፤ ምክንያቱም ፍርዱ የአንድን ሰው ኀጢአት ተከትሎ ኵነኔን አመጣ፤ ስጦታው ግን አያሌ መተላለፍን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ። በአንድ ሰው መተላለፍ ምክንያት ሞት በዚህ ሰው በኩል የነገሠ ከሆነ፣ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅ ስጦታ የተቀበሉት፣ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዴት አብልጠው በሕይወት አይነግሡ! ከእንግዲህ በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ኵነኔ በሁሉ ሰው ላይ እንደ መጣ፣ እንዲሁም በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ጽድቅ ተገኘ። በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። ሕግ በመምጣቱ መተላለፍ በዛ፤ ነገር ግን ኀጢአት በበዛበት ጸጋ አብልጦ የተትረፈረፈ ሆነ፤ ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደ ነገሠ ሁሉ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ እንዲነግሥ ነው።

ሮሜ 5:6-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን። ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤ ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቍኦጠርም፤ ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና። ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ። አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ። በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።

ሮሜ 5:6-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ገና ደካሞች ሆነን ሳለ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞተ። በጻድቅ ምትክ ሆኖ የሚሞት ሰው ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም በደግ ሰው ምትክ ለመሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል። እንግዲህ የጸደቅነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሆነ ይበልጡንም ከእግዚአብሔር ቊጣ የምንድነው በእርሱ አማካይነት ነው። እኛ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ሳለ በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል፤ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን በኋላ በልጁ ሕይወት አማካይነት ይበልጡን እንድናለን። ይህም ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነትም በእግዚአብሔር እንመካለን። በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአት ምክንያትም ሞት መጣ፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ኃጢአትን ስለ ሠራ ሞት በሰው ሁሉ ላይ መጣ፤ የሙሴ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ነበር፤ ይሁን እንጂ ሕግ በሌለበት ኃጢአት ራሱ እንደ ኃጢአት አይቈጠርም ነበር። ሆኖም እንደ አዳም ሕግን በመተላለፍ ኃጢአት ባልሠሩት ላይ እንኳ ሳይቀር ሞት ከአዳም አንሥቶ እስከ ሙሴ ድረስ በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን አገኘ። ይህ አዳም ወደፊት ለሚመጣው ክርስቶስ ምሳሌ ነበረ። ነገር ግን የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታው እንደ ሰው ኃጢአት አይደለም፤ በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ብዙዎች እንደ ሞቱ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት የተገኘው የጸጋ ስጦታ ለብዙዎች ተትረፍርፎ ተሰጥቶአል። እንዲሁም የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታው ያመጣው ጸጋ ውጤት የአንድ ሰው ኃጢአት እንዳመጣው ውጤት አይደለም። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ፍርድ ቅጣትን አመጣ፤ በብዙ ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ነጻ ስጦታ ጽድቅን አመጣ። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ሞት በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን ካገኘ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና ነጻ ስጦታ ተቀብለው የጸደቁ ሁሉ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በድል አድራጊነት በሕይወት ይኖራሉ። እንግዲህ የአንዱ የአዳም ኃጢአት የቅጣትን ፍርድ በሰው ሁሉ ላይ እንዳመጣ እንዲሁም የአንዱ የክርስቶስ የጽድቅ ሥራ ብዙዎችን ከቅጣት ነጻ አድርጎ ሕይወትን ይሰጣል። በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁም በክርስቶስ መታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ይጸድቃሉ። ኃጢአት ይበዛ ዘንድ ሕግ መጣ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛ መጠን የእግዚአብሔር ጸጋ በይበልጥ በዛ። ይህም የሆነው በሞት ምክንያት ኃጢአት እንደ ነገሠ ሁሉ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን በመስጠት ይነግሣል።

ሮሜ 5:6-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ገና ደካሞች ሳለን፥ በትክክለኛው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቷልና። ስለ ጻድቅ ሰው ሲል የሚሞት ሰው ማግኘት አስቸጋሪ ነው፤ ስለ መልካም ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን ይበልጡንም በእርሱ በኩል ከቁጣ እንድናለን። ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን። ስለዚህ ኃጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ፥ ሞትም በኃጢአት በኩል እንደመጣ፥ እንዲሁም ሁሉም ኃጢአትን ስለ ሠሩ፥ ሞት በሰው ሁሉ ላይ መጣ፤ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ነበረና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም። ነገር ግን ለሚመጣው ምሳሌ እንደነበረው እንደ አዳም ሕግን ባልተላለፉት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ። ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ከሞቱ፥ ይልቁንም የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ያለው ስጦታ ለብዙዎች እንዴት ይበዛ። ስጦታውም አንድ ሰው ኃጢአትን በማድረጉ እንዳመጣው ውጤት አይደለም፤ በአንድ በኩል፥ ፍርዱ የአንድን ሰው በደል ተከትሎ ኩነኔን አመጣ፤ በሌላ በኩል ግን ስጦታው ብዙ በደልን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ። በአንድ ሰው በደል ምክንያት በዚህ ሰው በኩል ሞት ከነገሠ፥ ይልቁን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅን ስጦታ የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። እንግዲህ በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኩነኔ ለሰው ሁሉ እንደመጣ፥ እንዲሁም በአንድ ሰው የጽድቅ ሥራ ምክንያት ሕይወትን ለማጽደቅ መጣ። በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ ሰው መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤ ይህም የሆነው፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘለዓለም ሕይወት፥ በጽድቅ በኩል እንዲነግሥ ነው።