የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 89

89
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የሙሴ ጸሎት።
1አቤቱ፥ አንተ ለልጅ ልጅ ሁሉ መጠ​ጊያ ሆን​ህ​ልን።
2ተራ​ሮች ሳይ​ወ​ለዱ፥ ምድ​ርም ዓለ​ምም ሳይ​ሠሩ፥
ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።
3ሰውን ወደ ኀሣር አት​መ​ል​ሰው፤
የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመ​ለሱ ትላ​ለህ፤
4ሺህ ዓመት በፊ​ትህ እን​ዳ​ለ​ፈች እንደ ትና​ንት ቀን፥
እንደ ሌሊ​ትም ሰዓት ነውና።
5ዘመ​ኖች በፊ​ትህ የተ​ናቁ ናቸው፥
በማ​ለ​ዳም እንደ ሣር ያል​ፋል።
6ማልዶ ይበ​ቅ​ላል#ዕብ. “ያብ​ባል” ይላል። ያል​ፋ​ልም፥
በሠ​ር​ክም ጠው​ል​ጎና ደርቆ ይወ​ድ​ቃል።
7እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥
በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመ​ዓ​ትህ” ይላል። ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።
8ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በፊ​ትህ አስ​ቀ​መ​ጥህ፥
ዓለ​ማ​ች​ንም በፊ​ትህ ብር​ሃን ነው።
9ዘመ​ና​ችን ሁሉ አል​ፎ​አ​ልና፥
እኛም በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመ​ዓ​ትህ” ይላል። አል​ቀ​ና​ልና፤
ዘመ​ኖ​ቻ​ች​ንም እንደ ሸረ​ሪት ድር ይሆ​ናሉ።
10የዘ​መ​ኖ​ቻ​ች​ንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥
ቢበ​ዛም ሰማ​ንያ ዓመት ነው፤
ከእ​ነ​ዚህ ቢበዛ ግን ድካ​ምና መከራ ነው፤
የዋ​ህ​ነት ከእኛ አል​ፋ​ለ​ችና፥ እኛም ተገ​ሥ​ጸ​ና​ልና።
11የመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ኀይል ማን ያው​ቃል?
ከቍ​ጣህ ግርማ የተ​ነሣ አለቁ።
12ጥበ​ብን በልብ ለተ​ማሩ፥
ቀኝ​ህን እን​ዲህ ግለጥ።
13አቤቱ፥ ተመ​ለስ፥ እስከ መቼስ ነው?
ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ተሟ​ገት።
14በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን እን​ጠ​ግ​ባ​ለ​ንና፤
በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ ደስ ይለ​ናል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን።
15መከ​ራን ባሳ​የ​ኸን ዘመን ፋንታ፥
ክፉ​ንም ባየ​ን​ባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለ​ናል።
16ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንና ሥራ​ህን እይ፥
ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምራ​ቸው።
17የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ይሁን።
የእ​ጆ​ቻ​ች​ን​ንም ሥራ ያቃ​ና​ል​ናል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ