መዝሙረ ዳዊት 89
89
የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት።
1አቤቱ፥ አንተ ለልጅ ልጅ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።
2ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።
3ሰውን ወደ ኀሣር አትመልሰው፤
የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመለሱ ትላለህ፤
4ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥
እንደ ሌሊትም ሰዓት ነውና።
5ዘመኖች በፊትህ የተናቁ ናቸው፥
በማለዳም እንደ ሣር ያልፋል።
6ማልዶ ይበቅላል#ዕብ. “ያብባል” ይላል። ያልፋልም፥
በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።
7እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥
በመቅሠፍትህም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመዓትህ” ይላል። ደንግጠናልና።
8ኀጢአታችንን በፊትህ አስቀመጥህ፥
ዓለማችንም በፊትህ ብርሃን ነው።
9ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥
እኛም በመቅሠፍትህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመዓትህ” ይላል። አልቀናልና፤
ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይሆናሉ።
10የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥
ቢበዛም ሰማንያ ዓመት ነው፤
ከእነዚህ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤
የዋህነት ከእኛ አልፋለችና፥ እኛም ተገሥጸናልና።
11የመቅሠፍትህን ኀይል ማን ያውቃል?
ከቍጣህ ግርማ የተነሣ አለቁ።
12ጥበብን በልብ ለተማሩ፥
ቀኝህን እንዲህ ግለጥ።
13አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው?
ስለ ባሪያዎችህም ተሟገት።
14በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለንና፤
በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።
15መከራን ባሳየኸን ዘመን ፋንታ፥
ክፉንም ባየንባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለናል።
16ባሪያዎችህንና ሥራህን እይ፥
ልጆቻቸውንም ምራቸው።
17የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን።
የእጆቻችንንም ሥራ ያቃናልናል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 89: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ