የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 63

63
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥
ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍር​ሀት” ይላል። ነፍ​ሴን አድ​ናት።
2ከክ​ፉ​ዎች ሴራ
ከብ​ዙ​ዎች ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ሰው​ረኝ።
3እንደ እባብ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰይፍ” ይላል። ምላ​ሳ​ቸ​ውን አሰሉ፤
መራራ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ፥
4ንጹ​ሕ​ንም በስ​ውር ለመ​ግ​ደል ቀስ​ትን ገተሩ፤
በድ​ን​ገት ይነ​ድ​ፏ​ቸ​ዋል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይነ​ድ​ፏ​ታል” ይላል። አይ​ፈ​ሩ​ምም።
5ለእ​ነ​ርሱ ለራ​ሳ​ቸው ክፉ ነገ​ርን አጸኑ፤
ወጥ​መ​ድን ይሰ​ውሩ ዘንድ ተማ​ከሩ፤
የሚ​ያ​ም​ንም የለም ይላሉ።
6ዐመ​ፃን ፈለ​ጓት፥
ሲፈ​ት​ኑም ሲጀ​ም​ሩም አለቁ፤
ሰው በጥ​ልቅ ልብ#ከዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል። ውስጥ ይገ​ባል፥
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፍ ከፍ ይላል።
መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው እንደ ልጆች ሕንፃ ሆነ፤#ዕብ. “የድ​ን​ገት ፍላጻ ይነ​ድ​ፋ​ቸ​ዋል” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቍስ​ላ​ቸው በል​ጆች ፍላጻ ሆነ” ይላል።
8አን​ደ​በ​ታ​ቸው በላ​ያ​ቸው ደከመ፥
የሚ​ያ​ዩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ደነ​ገጡ።
9ሰው ሁሉ ፈራ፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ ተና​ገሩ፥
ሥራ​ው​ንም ዐወቁ።
10ጻድቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፥ በእ​ር​ሱም ይታ​መ​ናል፤
ልባ​ቸ​ውም የቀና ሁሉ ይከ​ብ​ራሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ