መዝሙረ ዳዊት 62
62
በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤
ነፍሴ አንተን ተጠማች፥
እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ
ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች” ይላል።
2ኀይልህንና ክብርህን ዐውቅ ዘንድ
እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።
3ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና፥
ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
4እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥
በአንተም ስም እጆችን አነሣለሁ።
5ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥
ደስተኞች ከንፈሮቼም ስምህን ያመሰግናሉ።
6በመኝታዬም አስብሃለሁ፥
በማለዳም እናገርልሃለሁ፤
7ረዳቴ ሆነኽልኛልና፥
በክንፎችህም ጥላ እታመናለሁ።
8ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥
እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።
9እነርሱ ግን ነፍሴን ለከንቱ ፈለጓት፤
ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ።
10በሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጡ፥
የቀበሮዎችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።
11ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤
በእርሱም የሚምል ሁሉ ይከብራል፥
ዐመፅን የሚናገር አፍ ይዘጋልና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 62: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ