መዝሙረ ዳዊት 58
58
ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ። ሳኦል ይገድሉት ዘንድ ቤቱን እንዲጠብቁ በላከ ጊዜ የዳዊት ቅኔ።
1አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶች አድነኝ፤
በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።
2ከዐመፅ አድራጊዎች ታደገኝ፥
ከደም ሰዎችም አድነኝ።
3እነሆ፥ ነፍሴን አድድነዋታልና፥
ብርቱዎችም በላዬ ተነሡ፤
አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኀጢአቴም አይደለም።
4ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፤
ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።
5አንተም አቤቱ፥ የኀያላን አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አምላክ” ይላል።
አሕዛብን ሁሉ ጐብኛቸው፥ ይቅርም በላቸው፤#ዕብ. “ትጎበኛቸው ዘንድ ንቃ” ይላል።
ዐመፅ የሚያደርጉትን ሁሉ ግን አትማራቸው።
6ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥
በከተማም ይዙሩ።
7እነሆ፥ በአፋቸው ይናገራሉ፤
ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤
8የምትሰማቸው#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ማን ይሰማል” ይላል። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥
አሕዛቡንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ፥
9ኀይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ፥
አንተ አምላኬና መጠጊያዬ ነህና።
10የአምላኬ ይቅርታው ይድረሰኝ
አምላኬ በጠላቶቼ ላይ አሳየኝ።
11ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፤
አቤቱ፥ አምላኬና ረዳቴ፥ በኀይልህ በትናቸው፥ አዋርዳቸውም።
12ስለ አፋቸው ኀጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥ በትዕቢታቸው ይጠመዱ
ከመርገማቸውና ከሐሰታቸው የተነሣ፥ ፍጻሜያቸው ይታወቃል።
13ኋላ በሚመጣ መቅሠፍት ያልቃሉ፤#ዕብ. “በቍጣ አጥፋቸው እንዳይኖሩም አጥፋቸው” ይላል።
የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንዲገዛ ይወቁ።
14ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥
በከተማም ይዙሩ።
15እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ፤
የጠገቡ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያልጠገቡ” ይላል። እንደ ሆነም ያንጐራጕራሉ።
16እኔ ግን ለኀይልህ እቀኛለሁ፤
በምሕረትህም በማለዳ ደስ ይለኛል፤
በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኽልኛልና።
17አንተ ረዳቴ ነህ፥ ለአንተም ለአምላኬ እዘምራለሁ፤
አንተ፥ አምላኬ፥ መጠጊያዬ ነህና አምላኪዬ ምሕረቴም ነህና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 58: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ