መዝሙረ ዳዊት 54
54
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት ትምህርት።
1አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጠኝ፥
ልመናዬንም ቸል አትበለኝ።
2ተመልከተኝ፥ ስማኝም፤
አዘንሁ፥ ደነገጥሁ፥ ተናወጥሁም፤
3ከጠላት ድምፅ፥ ከኀጢአተኛም ማሠቃየት የተነሣ፥
ዐመፃን በላዬ መልሰውብኛልና፥ ሊያጠፉኝም ተነሥተውብኛልና።
4ልቤ በላዬ ደነገጠብኝ፥
የሞት ድንጋጤም መጣብኝ።
5ፍርሃትና እንቅጥቅጥ ያዙኝ፥
ጨለማም ሸፈነኝ።
6በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ አልሁ፥
7እነሆ፥ ኮብልዬ በራቅሁ፥ በምድረ በዳም በኖርሁ፤
8እንደ ዐውሎ ነፋስ ከሆነው #ዕብ. “ከነፍሴ መቅበዝበዝ የሚያድነኝን ተስፋ አደርገዋለሁ” የሚለው በዕብ. የለም።ከነፍሴ መቅበዝበዝ የሚያድነኝን ተስፋ አደርገዋለሁ።
9አቤቱ፥ ዐመፃንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይችአለሁና
አስጥማቸው፥ አንደበታቸውንም ቍረጥ።
10በቀንና በሌሊት በቅጥርዋ ይከብቡአታል፤
ዐመፃና ድካም ኀጢአትም በመካከልዋ ነው፤
11ሽንገላ#ዕብ. “ተንኰልና ሽንገላ” ይላል። ከአደባባይዋ አይርቅም።
12ጠላትስ ቢሰድበኝ፥ በታገሥሁ ነበር፤
የሚጠላኝም አፉን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ፥
ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።
13አንተ ሰው፥ አንተ ግን እንደ ራሴ ነበርህ፥
ባልንጀራዬና የማውቅህ ወዳጄም ነበርህ፤
14መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ ነበርህ፤
በአንድ ልብ ወደ እግዚአብሔር ቤት ተራመድን።
15ሞት ይምጣባቸው፤
በሕይወት ሳሉም ወደ ሲኦል ይውረዱ፤
ክፋት በማደሪያቸውና በመካከላቸው ነውና።
16እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥
እግዚአብሔርም ሰማኝ።
17በማታና በጥዋት በቀትርም እናገራለሁ
አስረዳለሁ፥ ቃሌንም አይሰሙኝም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እርሱም ይሰማኛል” ይላል።
18ከእኔ ጋር ካሉት ይበዛሉና
ከሚቃረቡኝ ነፍሴን በሰላም አድናት።
19ቤዛ የላቸውምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና
ዓለም ሳይፈጠር የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቍላቸዋል።
20ፍዳን ለማምጣት#ዕብ. ይለያል። እጁን ዘረጋ፤ ኪዳኑንም አረከሱ።
21ከፊቱም ቍጣ የተነሣ ተለያዩ፥ ልቡም ቀረበ፤#ዕብ. “በልቡ ሰልፍ ነበረ” ይላል።
ቃሉም ከቅቤ ይልቅ ለሰለሰ፤
እነርሱ ግን እንደሚያሰጥም ማዕበል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰይፍ” ይላል። ናቸው።
22ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል፥
እርሱም ይመግብሃል፤
ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።
23አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ወደ ሞት ጕድጓድ አውርዳቸው፤
የደም ሰዎችና ሸንጋዮች ዘመናቸውን አያጋምሱም፤#የግእዙ ልዩ ነው።
እኔ ግን፥ አቤቱ እታመንሃለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 54: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ