የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 55

55
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ከቅ​ዱ​ሳን ስለ ራቁ ሕዝብ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በጌት በያ​ዙት ጊዜ የዳ​ዊት ቅኔ።
1አቤቱ፥ ሰው ረግ​ጦ​ኛ​ልና ይቅር በለኝ፤
ሁል​ጊ​ዜም ሰልፍ አስ​ጨ​ን​ቆ​ኛል።
2ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ጠላ​ቶች ረገ​ጡኝ፥
የሚ​ዋ​ጉኝ በዝ​ተ​ዋ​ልና ፈራሁ።
3እኔ ግን አቤቱ በአ​ንተ ታመ​ንሁ።
4በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሉን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሉን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ” ይላል።
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ፥ አል​ፈ​ራም፤ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?
5ሁል​ጊዜ ቃሎ​ችን ይጸ​የ​ፉ​ብ​ኛል፤
በእኔ ላይም የሚ​መ​ክ​ሩት ሁሉ ለክፉ ነው።
6ይሸ​ም​ቁ​ብ​ኛል፥ ይሸ​ሸ​ጉ​ኝ​ማል፥
እነ​ር​ሱም ተረ​ከ​ዜን ይመ​ለ​ካ​ከ​ታሉ፥
ሁል​ጊ​ዜም ነፍ​ሴን ይሸ​ም​ቁ​ባ​ታል።
7በም​ንም ምን አታ​ድ​ና​ቸ​ውም፤
አሕ​ዛ​ብን በመ​ዓ​ትህ ትጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።
8አም​ላኬ ሆይ፥ ሕይ​ወ​ቴን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤
እን​ባ​ዬ​ንም እንደ ትእ​ዛ​ዝህ በፊ​ትህ አኖ​ርሁ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አኖ​ርህ” ይላል።
9በጠ​ራ​ሁህ ጊዜ ጠላ​ቶች ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ፤
አንተ አም​ላኬ እንደ ሆንህ እነሆ፥ ዐወ​ቅሁ።
10በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃሌን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤
የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይከ​ብ​ራል።#ከዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. ይለ​ያል።
11በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?
12አቤቱ፥ የም​ስ​ጋና ስእ​ለት የም​ሰ​ጥህ ከእኔ ዘንድ ነው፤
13ነፍ​ሴን ከሞት፥ ዐይ​ኖ​ቼን ከዕ​ንባ፥ እግ​ሮቼ​ንም ከድጥ አድ​ነ​ሃ​ልና፥
በሕ​ያ​ዋን ሀገር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ብር​ሃን” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው ዘንድ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ