የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 54

54
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በበ​ገ​ና​ዎች የዳ​ዊት ትም​ህ​ርት።
1አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ም​ጠኝ፥
ልመ​ና​ዬ​ንም ቸል አት​በ​ለኝ።
2ተመ​ል​ከ​ተኝ፥ ስማ​ኝም፤
አዘ​ንሁ፥ ደነ​ገ​ጥሁ፥ ተና​ወ​ጥ​ሁም፤
3ከጠ​ላት ድምፅ፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኛም ማሠ​ቃ​የት የተ​ነሣ፥
ዐመ​ፃን በላዬ መል​ሰ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ሊያ​ጠ​ፉ​ኝም ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና።
4ልቤ በላዬ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፥
የሞት ድን​ጋ​ጤም መጣ​ብኝ።
5ፍር​ሃ​ትና እን​ቅ​ጥ​ቅጥ ያዙኝ፥
ጨለ​ማም ሸፈ​ነኝ።
6በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክን​ፍን ማን በሰ​ጠኝ አልሁ፥
7እነሆ፥ ኮብ​ልዬ በራ​ቅሁ፥ በም​ድረ በዳም በኖ​ርሁ፤
8እንደ ዐውሎ ነፋስ ከሆ​ነው #ዕብ. “ከነ​ፍሴ መቅ​በ​ዝ​በዝ የሚ​ያ​ድ​ነ​ኝን ተስፋ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ” የሚ​ለው በዕብ. የለም።ከነ​ፍሴ መቅ​በ​ዝ​በዝ የሚ​ያ​ድ​ነ​ኝን ተስፋ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።
9አቤቱ፥ ዐመ​ፃ​ንና ጠብን በከ​ተማ ውስጥ አይ​ች​አ​ለ​ሁና
አስ​ጥ​ማ​ቸው፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ው​ንም ቍረጥ።
10በቀ​ንና በሌ​ሊት በቅ​ጥ​ርዋ ይከ​ብ​ቡ​አ​ታል፤
ዐመ​ፃና ድካም ኀጢ​አ​ትም በመ​ካ​ከ​ልዋ ነው፤
11ሽን​ገላ#ዕብ. “ተን​ኰ​ልና ሽን​ገላ” ይላል። ከአ​ደ​ባ​ባ​ይዋ አይ​ር​ቅም።
12ጠላ​ትስ ቢሰ​ድ​በኝ፥ በታ​ገ​ሥሁ ነበር፤
የሚ​ጠ​ላ​ኝም አፉን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያ​ደ​ርግ፥
ከእ​ርሱ በተ​ሸ​ሸ​ግሁ ነበር።
13አንተ ሰው፥ አንተ ግን እንደ ራሴ ነበ​ርህ፥
ባል​ን​ጀ​ራ​ዬና የማ​ው​ቅህ ወዳ​ጄም ነበ​ርህ፤
14መብ​ልን ከእኔ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ያጣ​ፈ​ጥህ ነበ​ርህ፤
በአ​ንድ ልብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተራ​መ​ድን።
15ሞት ይም​ጣ​ባ​ቸው፤
በሕ​ይ​ወት ሳሉም ወደ ሲኦል ይው​ረዱ፤
ክፋት በማ​ደ​ሪ​ያ​ቸ​ውና በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነውና።
16እኔ ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማኝ።
17በማ​ታና በጥ​ዋት በቀ​ት​ርም እና​ገ​ራ​ለሁ
አስ​ረ​ዳ​ለሁ፥ ቃሌ​ንም አይ​ሰ​ሙ​ኝም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እር​ሱም ይሰ​ማ​ኛል” ይላል።
18ከእኔ ጋር ካሉት ይበ​ዛ​ሉና
ከሚ​ቃ​ረ​ቡኝ ነፍ​ሴን በሰ​ላም አድ​ናት።
19ቤዛ የላ​ቸ​ው​ምና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ሩ​ት​ምና
ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር የነ​በረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰምቶ ያጐ​ሰ​ቍ​ላ​ቸ​ዋል።
20ፍዳን ለማ​ም​ጣት#ዕብ. ይለ​ያል። እጁን ዘረጋ፤ ኪዳ​ኑ​ንም አረ​ከሱ።
21ከፊ​ቱም ቍጣ የተ​ነሣ ተለ​ያዩ፥ ልቡም ቀረበ፤#ዕብ. “በልቡ ሰልፍ ነበረ” ይላል።
ቃሉም ከቅቤ ይልቅ ለሰ​ለሰ፤
እነ​ርሱ ግን እን​ደ​ሚ​ያ​ሰ​ጥም ማዕ​በል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰይፍ” ይላል። ናቸው።
22ትካ​ዜ​ህን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ጣል፥
እር​ሱም ይመ​ግ​ብ​ሃል፤
ለጻ​ድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሁከ​ትን አይ​ሰ​ጠ​ውም።
23አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ወደ ሞት ጕድ​ጓድ አው​ር​ዳ​ቸው፤
የደም ሰዎ​ችና ሸን​ጋ​ዮች ዘመ​ና​ቸ​ውን አያ​ጋ​ም​ሱም፤#የግ​እዙ ልዩ ነው።
እኔ ግን፥ አቤቱ እታ​መ​ን​ሃ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ