መዝሙረ ዳዊት 41
41
ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች ትምህርት።
1ዋሊያ ወደ ውኃ ምንጮች እንደሚናፍቅ፥
እንዲሁ ነፍሴ ወደ እግዚአብሔር ትናፍቃለች።
2ነፍሴ ወደ ሕያው አምላኬ ተጠማች፤
መቼ እደርሳለሁ? የአምላኬንስ ፊት መቼ አያለሁ?
3ዘወትር፥ “አምላክህ ወዴት ነው?” ይሉኛልና
እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።
4ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥
ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤
በዓልን የሚያደርጉ ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ።
5ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ?
የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ
በእግዚአብሔር ታመኚ።
6ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፤
ስለዚህ አቤቱ በዮርዳኖስ ምድር፥
በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ።
7በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራዋለች፤
ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
8እግዚአብሔር በቀን ይቅርታውን ያዝዛል፥
በሌሊትም እርሱን ይናገራል፤#ዕብ. “በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል” ይላል።
ከእኔ ዘንድ የሕይወቴ ብፅዐት ለእግዚአብሔር ነው።
9እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ#ዕብ. “ዐለቴ” ይላል። ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ?
ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?”
ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
10ሁልጊዜ፥ “አምላክህ ወዴት ነው?” ይሉኛልና።
11ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ?
የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ
በእግዚአብሔር ታመኚ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 41: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ