የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 39

39
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በት​ዕ​ግ​ሥት ደጅ ጠና​ሁት፥
እር​ሱም ተመ​ልሶ ሰማኝ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ሰማኝ።
2ከጥ​ፋት ጕድ​ጓድ ከረ​ግ​ረግ ጭቃም አወ​ጣኝ፥
እግ​ሮ​ቼ​ንም በዓ​ለት ላይ አቆ​ማ​ቸው፥
አረ​ማ​መ​ዴ​ንም አጸና።
3አዲስ ምስ​ጋ​ናን በአፌ ጨመረ፥ ይህም የአ​ም​ላ​ካ​ችን ምስ​ጋ​ናው ነው፤
ብዙ​ዎች አይ​ተው ይፍሩ፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይታ​መኑ።
4መታ​መ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሆነ፥
ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰ​ትም፥
ያል​ተ​መ​ለ​ከተ ሰው ብፁዕ ነው።
5አቤቱ አም​ላኬ፥ ብዙ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አደ​ረ​ግህ፥
አሳ​ብ​ህ​ንም ምንም የሚ​መ​ስ​ለው የለም፤
አወ​ራሁ፥ ተና​ገ​ርሁ፥ ከቍ​ጥ​ርም በዛ።
6መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አል​ወ​ደ​ድ​ህም” ይላል።
ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤#ዕብ. “ጆሮ​ህን ክፈ​ት​ልኝ” ይላል።
የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።#ዕብ. “አል​ወ​ደ​ድ​ህም” ይላል።
7በዚ​ያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤
ስለ እኔ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ተጽ​ፎ​አል፤
8አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን ለማ​ድ​ረግ መከ​ርሁ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወደ​ድሁ” ይላል።
ሕግ​ህም በልቤ ውስጥ ነው።”
9በታ​ላቅ ጉባኤ ጽድ​ቅ​ህን አወ​ራሁ፤
እነሆ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤
አቤቱ፥ አንተ ጽድ​ቄን ታው​ቃ​ለህ።
10ቅን​ነ​ት​ህን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እው​ነ​ት​ህን” ይላል። በልቤ ውስጥ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም፥
ማዳ​ን​ህ​ንም ተና​ገ​ርሁ፤ ይቅ​ር​ታ​ህ​ንና ምሕ​ረ​ት​ህን ከታ​ላቅ ጉባኤ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም።
11አቤቱ አንተ ይቅ​ር​ታ​ህን ከእኔ አታ​ርቅ፤
ቸር​ነ​ት​ህና እው​ነ​ትህ ዘወ​ትር ያግ​ኙኝ።
12ቍጥር የሌ​ላት ክፋት አግ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና፤
ኀጢ​አ​ቶቼ ተገ​ና​ኙኝ፥ ማየ​ትም ተስ​ኖ​ኛል፤
ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
13አቤቱ፥ ታድ​ነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍጠን” ይላል።
14ነፍ​ሴን ለማ​ጥ​ፋት የሚ​ወ​ድዱ ይፈሩ፥
በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይጐ​ስ​ቍሉ፤
በእኔ ላይ ክፋ​ትን ለማ​ድ​ረግ የሚ​ወ​ድዱ
ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ ይፈ​ሩም።#ዕብ. “ይጐ​ስ​ቍ​ሉም” ይላል።
15እሰይ፥ እሰይ የሚ​ሉኝ
እፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ወዲ​ያ​ውኑ ይከ​ፈሉ።
16አቤቱ፥ የሚ​ፈ​ል​ጉህ ሁሉ
በአ​ንተ ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ሐሤ​ት​ንም ያድ​ርጉ፤
ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወዱ
ዘወ​ትር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
17እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ያስ​ብ​ል​ኛል፤
አንተ ረዳ​ቴና መድ​ኀ​ኒቴ ነህ፤
አም​ላኬ ሆይ፥ አት​ዘ​ግይ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}