የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 38

38
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ለኤ​ዶ​ታም የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1“በአ​ን​ደ​በቴ እን​ዳ​ል​ስት አፌን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መን​ገ​ዴን” ይላል። እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤
ኃጥ​ኣን በፊቴ በተ​ቃ​ወ​ሙኝ ጊዜ
በአፌ ላይ ጠባቂ አኖ​ራ​ለሁ” አልሁ፤
2ዝም አልሁ ራሴ​ንም አዋ​ረ​ድሁ፥
ለበጎ ነገ​ርም ዝም አልሁ፥
ቍስ​ሌም ታደ​ሰ​ብኝ።
3ልቤም በው​ስጤ ሞቀ​ብኝ፤
ከመ​ና​ገ​ሬም የተ​ነሣ እሳት ነደደ፥
በአ​ን​ደ​በ​ቴም ተና​ገ​ርሁ፦
4“አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥
የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው?
ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?
5እነሆ፥ ዘመ​ኖቼን አስ​ረ​ጀ​ሃ​ቸው፤
አካ​ሌም በፊ​ትህ እንደ ኢም​ንት ነው።
ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።
6ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመ​ላ​ለ​ሳል፥
ነገር ግን በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ።#ዕብ​ራ​ይ​ስጥ በነ​ጠላ ቁጥር።
ያከ​ማ​ቻሉ የሚ​ሰ​በ​ስ​ቡ​ለ​ት​ንም አያ​ው​ቁም።
7አሁ​ንስ ተስ​ፋዬ ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን?
ትዕ​ግ​ሥ​ቴም ከአ​ንተ ዘንድ ነው።
8ከኀ​ጢ​አቴ ሁሉ አዳ​ን​ኸኝ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አድ​ነኝ” ይላል።
ለሰ​ነ​ፎ​ችም ስድብ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።
9ዝም አልሁ አፌ​ንም አል​ከ​ፈ​ት​ሁም።
አንተ ፈጥ​ረ​ኸ​ኛ​ልና፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሠር​ተ​ህ​ል​ኛ​ልና” ይላል።
10መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ከእኔ አርቅ፥
ከእ​ጅህ ብር​ታት የተ​ነሣ አል​ቄ​አ​ለ​ሁና።
11በተ​ግ​ሣ​ጽህ ስለ ኀጢ​አቱ ሰውን ዘለ​ፍ​ኸው፥
ሰው​ነ​ቱ​ንም እንደ ሸረ​ሪት አቀ​ለ​ጥ​ኻት፤
ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ።#ዕብ. “ሰው ሁሉ ከንቱ ነው” ይላል።
12አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥
ልቅ​ሶ​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ቸልም አት​በ​ለኝ፤
እኔ በም​ድር ላይ መጻ​ተኛ ነኝና፥
እንደ አባ​ቶ​ችም ሁሉ እን​ግዳ ነኝና።
13ወደ​ማ​ል​መ​ለ​ስ​በት ሳል​ሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ