የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 37

37
ለሰ​ን​በት መታ​ሰ​ቢያ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ አት​ቅ​ሠ​ፈኝ፥
በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አት​ገ​ሥ​ጸኝ።
2ፍላ​ጾ​ችህ ወግ​ተ​ው​ኛ​ልና፥
እጅ​ህ​ንም በእኔ ላይ አክ​ብ​ደ​ህ​ብ​ኛ​ልና።
3ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤
ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።
4ኀጢ​አቴ ከራሴ ጠጕር በዝ​ቷ​ልና፥
እንደ ከባድ ሸክ​ምም በላዬ ከብ​ዶ​አ​ልና።
5ከስ​ን​ፍ​ና​ዬም ፊት የተ​ነሣ አጥ​ን​ቶቼ ሸተቱ፥ በሰ​በ​ሱም፤
6እጅግ ጐሰ​ቈ​ልሁ፥ ጐበ​ጥ​ሁም፥
ሁል​ጊ​ዜም በት​ካዜ እመ​ላ​ለ​ሳ​ለሁ፤
7ነፍሴ ስድ​ብን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥
ለሥ​ጋ​ዬም ድኅ​ነ​ትን አጣሁ።
8ታመ​ምሁ እጅ​ግም ተሠ​ቃ​የሁ፥
ከል​ቤም ኀዘን የተ​ነሣ እጮ​ኻ​ለሁ።
9አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊ​ትህ ነው፥
ጩኸ​ቴም ከአ​ንተ አይ​ሰ​ወ​ርም።
10ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፥ ኀይ​ሌም ተወኝ፥
የዐ​ይ​ኖ​ቼም ብር​ሃን ፈዘ​ዘ​ብኝ።
11ወዳ​ጆቼም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቼም#ዕብ. “ወዳ​ጆ​ቼም ባል​ን​ጀ​ሮቼም ከቍ​ስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥ ዘመ​ዶ​ቼም ርቀው ቆሙ” ይላል። ባላ​ጋራ ሆኑኝ፥ ከበ​ውም ደበ​ደ​ቡኝ፥
ዘመ​ዶቼም ተስፋ ቈር​ጠው ተለ​ዩኝ።
12ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በረ​ቱ​ብኝ፥
መከ​ራ​ዬ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ከን​ቱን ተና​ገሩ፥
ሁል​ጊ​ዜም ያጠ​ፉኝ ዘንድ በሽ​ን​ገላ ይመ​ክ​ራሉ።
13እኔ ግን እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ደን​ቆሮ፥
አፉ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ፍት ዲዳ ሆንሁ።
14እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ሰው፥
በአ​ፉም መና​ገር እን​ደ​ማ​ይ​ችል ሰው ሆንሁ።
15አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና፤
አቤቱ አም​ላኬ፥ አንተ ስማኝ።
16የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አታ​ድ​ር​ገኝ ብያ​ለ​ሁና፥
እግ​ሬም ቢሰ​ና​ከል በእኔ ላይ ብዙ ነገ​ርን ይና​ገ​ራሉ።
17እኔ​ንስ ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ አቈ​ዩኝ፥
ቍስሌ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።
18በደ​ሌን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፥
ስለ ኀጢ​አ​ቴም እተ​ክ​ዛ​ለሁ።
19ጠላ​ቶቼ ሕያ​ዋን ናቸው፥ ይበ​ረ​ቱ​ብ​ኛ​ልም፥
በዐ​መ​ፃም የሚ​ጠ​ሉኝ በዙ።
20በበጎ ፋንታ ክፉን የሚ​መ​ል​ሱ​ልኝ
ጽድ​ቅን ስለ ተከ​ተ​ልሁ ይከ​ስ​ሱ​ኛል።
እንደ ርኩስ በድን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን ጣሉ፥#“እንደ ርኩስ በድን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን ጣሉ” የሚ​ለው በዕብ. የለም።
21አቤቱ፥ አንተ አት​ጣ​ለኝ፤
አም​ላኬ፥ ከእኔ አት​ራቅ።
22አቤቱ፥ የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ ሆይ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ፍጠን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}