የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 20

20
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ ንጉሥ ደስ ይለ​ዋል፤
በማ​ዳ​ን​ህም እጅግ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።
2የል​ቡን ፈቃድ ሰጠ​ኸው፥
የከ​ን​ፈ​ሮ​ቹ​ንም ልመና አል​ከ​ለ​ከ​ል​ኸ​ውም።
3በበጎ በረ​ከት ደር​ሰ​ህ​ለ​ታ​ልና፤
ከክ​ቡር ዕንቍ የሆነ ዘው​ድ​ንም በራሱ ላይ አኖ​ርህ።
4ሕይ​ወ​ትን ለመ​ነህ፥ ሰጠ​ኸ​ውም፥
ለረ​ዥም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ።
5በማ​ዳ​ንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤
ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ጨመ​ር​ህ​ለት።
6የዘ​ለ​ዓ​ለም በረ​ከ​ትን ሰጥ​ተ​ኸ​ዋ​ልና፥
በፊ​ት​ህም ደስታ ደስ ታሰ​ኘ​ዋ​ለህ።
7ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥
በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።
8እጅህ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው፥
ቀኝ​ህም የሚ​ጠ​ሉ​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው።
9ፊትህ በተ​ቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድ​ር​ጋ​ቸው፤
አቤቱ፥ በቍ​ጣህ አው​ካ​ቸው፥ እሳ​ትም ትብ​ላ​ቸው።
10ፍሬ​ያ​ቸ​ውን ከም​ድር፥
ዘራ​ቸ​ው​ንም ከሰው ልጆች አጥፋ።
11ክፋ​ትን በአ​ንተ ላይ ዘር​ግ​ተ​ዋ​ልና፥
መወ​ሰን የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ንም ምክር ዐሰቡ።
12ወደ ኋላ​ቸው ትመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤
ፊታ​ቸ​ውን ለመ​ዓ​ትህ ጊዜ#ዕብ. “ፍላ​ጻን በፊ​ታ​ቸው ላይ..” ይላል። ታዘ​ጋ​ጃ​ለህ።
13አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ ከፍ ከፍ አልህ፤
ጽና​ት​ህ​ንም እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን፤ እን​ዘ​ም​ር​ማ​ለን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ