የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 19

19
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1በመ​ከ​ራህ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይስ​ማህ፤
የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ስምም ይቁ​ም​ልህ።
2ከመ​ቅ​ደሱ ረድ​ኤ​ትን ይላ​ክ​ልህ፥
ከጽ​ዮ​ንም ይቀ​በ​ልህ።
3መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን#ዕብ. “ቍር​ባን” ይላል። ያስ​ብ​ልህ፤
ቍር​ባ​ን​ህ​ንም#ዕብ. “የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት” ይላል። ያለ​ም​ል​ም​ልህ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ልብህ ይስ​ጥህ
ፈቃ​ድ​ህ​ንም ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ልህ።
5በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ናል፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላ​ካ​ችን ስም ከፍ ከፍ እን​ላ​ለን፤
ልመ​ና​ህን ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ጽ​ም​ልህ።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እን​ዳ​ዳ​ነው ዛሬ ዐወ​ቅሁ፤
ከሰ​ማይ መቅ​ደሱ ይመ​ል​ስ​ለ​ታል
በቀኙ የማ​ዳን ኀይል።
7እነ​ዚያ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ላ​ዎች ይታ​መ​ናሉ፤
እኛ ግን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከፍ ከፍ እን​ላ​ለን።
8እነ​ርሱ ተሰ​ነ​ካ​ክ​ለው ወደቁ፤
እኛ ግን ተነ​ሣን፥ ጸን​ተ​ንም ቆምን።
9አቤቱ፥ ንጉ​ሥን አድ​ነው፥
በም​ን​ጠ​ራ​ህም ቀን ስማን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ