የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 143:7-12

መዝ​ሙረ ዳዊት 143:7-12 አማ2000

እጅ​ህን ከአ​ር​ያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድ​ነኝ፤ ከባ​ዕድ ልጆ​ችም እጅ፥ አፋ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ አስ​ጥ​ለኝ። አቤቱ፥ በአ​ዲስ ምስ​ጋና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዐሥር አው​ታር ባለው በገ​ናም እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ። ለነ​ገ​ሥ​ታት መድ​ኀ​ኒ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ባሪ​ያው ዳዊ​ትን ከክፉ ጦር የሚ​ያ​ድ​ነው እርሱ ነው። አፋ​ቸ​ውም ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ፥ ከባ​ዕድ ልጆች እጅ አድ​ነኝ፥ አስ​ጥ​ለ​ኝም። ልጆ​ቻ​ቸው በጐ​ል​ማ​ስ​ነ​ታ​ቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እል​ፍኝ ያማ​ሩና ያጌጡ፤