የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 131

131
የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ ዳዊ​ትን፥ ገር​ነ​ቱ​ንም ሁሉ ዐስብ፤
2ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ፥
ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እንደ ተሳለ፦
3“ወደ ቤቴ ድን​ኳን አል​ገ​ባም፥
ወደ መኝ​ታ​ዬም አልጋ አል​ወ​ጣም፥
4ለዐ​ይ​ኖቼም መኝ​ታን፥ ለቅ​ን​ድ​ቦ​ቼም እን​ቅ​ል​ፍን፥
ለጕ​ን​ጮ​ቼም ዕረ​ፍ​ትን አል​ሰ​ጥም፥
5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቦታ፥
የያ​ዕ​ቆብ አም​ላ​ክን ማደ​ሪያ እስ​ካ​ገኝ ድረስ” ብሎ እንደ ተሳለ ዐስብ።
6እነሆ፥ በኤ​ፍ​ራታ ሰማ​ነው፥
ዛፍ በበ​ዛ​በ​ትም ቦታ አገ​ኘ​ነው።
7እን​ግ​ዲ​ህስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እን​ገ​ባ​ለን፤
የጌ​ታ​ችን እግ​ሮቹ በሚ​ቆ​ሙ​በት ቦታ እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን።
8አቤቱ፥ ወደ ዕረ​ፍ​ትህ ተነሥ፥
አን​ተና የመ​ቅ​ደ​ስህ ታቦት።
9ካህ​ና​ትህ ጽድ​ቅን ይለ​ብ​ሳሉ፥
ጻድ​ቃ​ን​ህም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
10ስለ ባሪ​ያህ ስለ ዳዊት
ቀብ​ተህ ካነ​ገ​ሥ​ኸው ፊት​ህን አት​መ​ልስ።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊት እን​ዲህ ሲል በእ​ው​ነት ማለ፥ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም፥
“ከሆ​ድህ ፍሬ በዙ​ፋ​ንህ ላይ አስ​ቀ​ም​ጣ​ለ​ሁና
12ልጆ​ችህ ኪዳ​ኔን፥
ይህ​ንም የማ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ሬን ቢጠ​ብቁ፥
ልጆ​ቻ​ቸው በዙ​ፋ​ንህ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቀ​መ​ጣሉ።”
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መር​ጦ​አ​ታ​ልና፥
ማደ​ሪ​ያ​ውም ትሆ​ነው ዘንድ ወድ​ዶ​አ​ታ​ልና፥
14“ይህች ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማረ​ፊ​ያዬ ናት፤
መር​ጫ​ታ​ለ​ሁና በዚ​ህች አድ​ራ​ለሁ።
15ባል​ቴ​ቶ​ች​ዋን እጅግ እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፥
ድሆ​ች​ዋ​ንም እህ​ልን አጠ​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥
16ካህ​ና​ቷ​ንም ደኅ​ን​ነ​ትን አለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፥
ጻድ​ቃ​ኖ​ች​ዋም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
17በዚያ ለዳ​ዊት ቀን​ድን አበ​ቅ​ላ​ለሁ፥
ቀብቼ ላነ​ገ​ሥ​ሁ​ትም መብ​ራ​ትን አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ።
18ጠላ​ቶ​ቹ​ንም እፍ​ረ​ትን አለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤
በእ​ር​ሱም ቅድ​ስ​ናዬ ያፈ​ራል።”#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያብ​ባል” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ