መዝሙረ ዳዊት 131
131
የመዓርግ መዝሙር።
1አቤቱ፥ ዳዊትን፥ ገርነቱንም ሁሉ ዐስብ፤
2ለእግዚአብሔር እንደ ማለ፥
ለያዕቆብም አምላክ እንደ ተሳለ፦
3“ወደ ቤቴ ድንኳን አልገባም፥
ወደ መኝታዬም አልጋ አልወጣም፥
4ለዐይኖቼም መኝታን፥ ለቅንድቦቼም እንቅልፍን፥
ለጕንጮቼም ዕረፍትን አልሰጥም፥
5የእግዚአብሔርን ቦታ፥
የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስካገኝ ድረስ” ብሎ እንደ ተሳለ ዐስብ።
6እነሆ፥ በኤፍራታ ሰማነው፥
ዛፍ በበዛበትም ቦታ አገኘነው።
7እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያዎች እንገባለን፤
የጌታችን እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንሰግዳለን።
8አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥
አንተና የመቅደስህ ታቦት።
9ካህናትህ ጽድቅን ይለብሳሉ፥
ጻድቃንህም ደስ ይላቸዋል።
10ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት
ቀብተህ ካነገሥኸው ፊትህን አትመልስ።
11እግዚአብሔር ለዳዊት እንዲህ ሲል በእውነት ማለ፥ አይጸጸትምም፥
“ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁና
12ልጆችህ ኪዳኔን፥
ይህንም የማስተምራቸውን ምስክሬን ቢጠብቁ፥
ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ ለዘለዓለም ይቀመጣሉ።”
13እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥
ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥
14“ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤
መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።
15ባልቴቶችዋን እጅግ እባርካቸዋለሁ፥
ድሆችዋንም እህልን አጠግባቸዋለሁ፥
16ካህናቷንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥
ጻድቃኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።
17በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥
ቀብቼ ላነገሥሁትም መብራትን አዘጋጃለሁ።
18ጠላቶቹንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤
በእርሱም ቅድስናዬ ያፈራል።”#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያብባል” ይላል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 131: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ