መዝሙረ ዳዊት 129
129
የመዓርግ መዝሙር።
1አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።
2አቤቱ፥ ቃሌን ስማኝ፤
ጆሮህም የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይሁን።
3አቤቱ፥ ኀጢአትንስ ብትጠባበቅ፥
አቤቱ፥ ማን ይቆማል?
4ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና።
5አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤
ነፍሴ በሕግህ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በቃልህ” ይላል። ታገሠች።
6ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት
ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች።
ከማለዳ ጀምሮ እስራኤል በእግዚአብሔር ታመነ።
7ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታ፥
በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን አለና፥
8እርሱም እስራኤልን ከኀጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 129: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ