መዝሙረ ዳዊት 117
117
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
2ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ሆነ፥
የእስራኤል ወገን ንገሩ።
3ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ሆነ፥
የአሮን ወገን ንገሩ።
4ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ሆነ፥
እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ንገሩ።
5በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤
ሰማኝ፥ አሰፋልኝም።
6እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?
7እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ እነሆ፥ በጠላቶቼ ላይ አያለሁ።
8በሰው ከመታመን በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
9በአለቆች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል።
10አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥
በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤
11መክበቡንስ ከበቡኝ፥
በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤
12ንብ ማርን እንደሚከብብ ከበቡኝ፥
እሳትም በእሾህ ውስጥ እንደሚነድድ ነደዱ፤
በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው።
13ለመውደቅም ተንገደገድሁ፤
እግዚአብሔር ግን አነሣኝ።
14ኀይሌም ስም አጠራሬም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝማሬዬ” ይላል። እግዚአብሔር ነው፥
እርሱም አዳኜ ሆነኝ።
15የደስታ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእልልታና የመድኀኒት” ይላል። ድምፅ በጻድቃን
ማደሪያዎች ነው
የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች።
16የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፤
የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች።
17አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥
የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።
18መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤
ለሞት ግን አሳልፎ አልሰጠኝም።
19የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤
ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግን ዘንድ።
20ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤
ወደ እርስዋ ጻድቃን ይገባሉ።
21ሰምተኸኛልና፥
አዳኜም ሆነኸኛልና አቤቱ፥#“አቤቱ” በግእዝ ብቻ። አመሰግንሃለሁ።
22ግንበኞች የናቋት ድንጋይ፥
እርሷ የማዕዘን ራስ ሆነች፥
23ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፥
ለዐይኖቻችንም ድንቅ ናት።
24እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤
በእርስዋ ደስ ይበለን፥ ሐሤትንም እናድርግባት።
25አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤
አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።
26በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤
ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።
27ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤
እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ
በሚያስተነትኑበት በደስታ በዓልን አድርጉ።
28አንተ አምላኬ ነህ፥ አመሰግንህማለሁ።
አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍም አደርግሃለሁ፤
ሰምተኸኛልና፥
አዳኜም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
29እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 117: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ