የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 117

117
ሃሌ ሉያ።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።
2ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሆነ፥
የእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ንገሩ።
3ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሆነ፥
የአ​ሮን ወገን ንገሩ።
4ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሆነ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ ሁሉ ንገሩ።
5በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራ​ሁት፤
ሰማኝ፥ አሰ​ፋ​ል​ኝም።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ነው፥ አል​ፈ​ራም፤ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ነው፥ እነሆ፥ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አያ​ለሁ።
8በሰው ከመ​ታ​መን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል።
9በአ​ለ​ቆች ተስፋ ከማ​ድ​ረግ ይልቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ ማድ​ረግ ይሻ​ላል።
10አሕ​ዛብ ሁሉ ከበ​ቡኝ፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም አሸ​ነ​ፍ​ኋ​ቸው፤
11መክ​በ​ቡ​ንስ ከበ​ቡኝ፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም አሸ​ነ​ፍ​ኋ​ቸው፤
12ንብ ማርን እን​ደ​ሚ​ከ​ብብ ከበ​ቡኝ፥
እሳ​ትም በእ​ሾህ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ ነደዱ፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም አሸ​ነ​ፍ​ኋ​ቸው።
13ለመ​ው​ደ​ቅም ተን​ገ​ደ​ገ​ድሁ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አነ​ሣኝ።
14ኀይ​ሌም ስም አጠ​ራ​ሬም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝማ​ሬዬ” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥
እር​ሱም አዳኜ ሆነኝ።
15የደ​ስታ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ል​ል​ታና የመ​ድ​ኀ​ኒት” ይላል። ድምፅ በጻ​ድ​ቃን
ማደ​ሪ​ያ​ዎች ነው
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ኀይ​ልን አደ​ረ​ገች።
16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገ​ችኝ፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ኀይ​ልን አደ​ረ​ገች።
17አል​ሞ​ትም በሕ​ይ​ወት እኖ​ራ​ለሁ እንጂ፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ እና​ገ​ራ​ለሁ።
18መገ​ሠ​ጽስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገሠ​ጸኝ፤
ለሞት ግን አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ኝም።
19የጽ​ድ​ቅን ደጆች ክፈ​ቱ​ልኝ፤
ወደ እነ​ርሱ ገብቼ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግን ዘንድ።
20ይህች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደጅ ናት፤
ወደ እር​ስዋ ጻድ​ቃን ይገ​ባሉ።
21ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥
አዳ​ኜም ሆነ​ኸ​ኛ​ልና አቤቱ፥#“አቤቱ” በግ​እዝ ብቻ። አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።
22ግን​በ​ኞች የና​ቋት ድን​ጋይ፥
እርሷ የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነች፥
23ይህች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆነች፥
ለዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ንም ድንቅ ናት።
24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራት ቀን ይህች ናት፤
በእ​ር​ስዋ ደስ ይበ​ለን፥ ሐሤ​ት​ንም እና​ድ​ር​ግ​ባት።
25አቤቱ፥ እባ​ክህ፥ አሁን አድን፤
አቤቱ፥ እባ​ክህ፥ አሁን አቅና።
26በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው፤
ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መረ​ቅ​ና​ችሁ።
27ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገ​ለ​ጠ​ልን፤
እስከ መሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ድረስ
በሚ​ያ​ስ​ተ​ነ​ት​ኑ​በት በደ​ስታ በዓ​ልን አድ​ርጉ።
28አንተ አም​ላኬ ነህ፥ አመ​ሰ​ግ​ን​ህ​ማ​ለሁ።
አንተ አም​ላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤
ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥
አዳ​ኜም ሆነ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።
29እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥
ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ