የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 114

114
ሃሌ ሉያ።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​መ​ና​ዬን ድምፅ ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ​ድ​ሁት።
2ጆሮ​ውን ወደ እኔ አዘ​ን​ብ​ሎ​አ​ልና
በዘ​መኔ ሁሉ እጠ​ራ​ዋ​ለሁ።
3የሞት ጣር ያዘኝ፥
የሲ​ኦ​ልም ሕማም አገ​ኘኝ፤ ጭን​ቀ​ትና መከራ አገ​ኘኝ።
4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራሁ፦
አቤቱ፥ ነፍ​ሴን አድ​ናት።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ጻድቅ ነው።
አም​ላ​ካ​ችን ይቅር ባይ ነው።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕፃ​ና​ትን#ዕብ. “የዋ​ሃ​ንን” ይላል። ይጠ​ብ​ቃል፤
ተቸ​ገ​ርሁ እር​ሱም አዳ​ነኝ።
7ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረ​ፍ​ትሽ ተመ​ለሺ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ትሽ ነውና፤
8ነፍ​ሴን ከሞት፥ ዓይ​ኔ​ንም ከእ​ንባ፥
እግ​ሬ​ንም ከድጥ አድ​ኖ​አ​ልና።
9በሕ​ያ​ዋን ሀገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው ዘንድ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ