መዝሙረ ዳዊት 115
115
1በተናገርሁት አመንሁ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ” ይላል።
እኔም እጅግ ታመምሁ።
2እኔም ከራሴ ጀምሮ፥ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
3ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምንን እከፍለዋለሁ?
4የሕይወትን ጽዋ እቀበላለሁ፥
የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
5በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ።#“በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ” የሚለው በግእዝ የለም።
6የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።
7አቤቱ፥ እኔ ባሪያህ ነኝ፥
ባሪያህ ነኝ፥ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ፤
ሰንሰለቴን ሰበርህ።
8ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለሁ፥
የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።#“የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ” የሚለው በግእዝ የለም።
9በሕዝቡ ሁሉ ፊት
ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ፥
10በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ፥
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በመካከልሽም።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 115: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ