የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 115

115
1በተ​ና​ገ​ር​ሁት አመ​ንሁ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አመ​ንሁ ስለ​ዚ​ህም ተና​ገ​ርሁ” ይላል።
እኔም እጅግ ታመ​ምሁ።
2እኔም ከራሴ ጀምሮ፥ “ሰው ሁሉ ሐሰ​ተኛ ነው” አልሁ።
3ስላ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምንን እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ?
4የሕ​ይ​ወ​ትን ጽዋ እቀ​በ​ላ​ለሁ፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።
5በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ስእ​ለ​ቴን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ጣ​ለሁ።#“በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ስእ​ለ​ቴን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ጣ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም።
6የጻ​ድቅ ሞት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የከ​በረ ነው።
7አቤቱ፥ እኔ ባሪ​ያህ ነኝ፥
ባሪ​ያህ ነኝ፥ የሴት ባሪ​ያ​ህም ልጅ ነኝ፤
ሰን​ሰ​ለ​ቴን ሰበ​ርህ።
8ለአ​ንተ የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።#“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም።
9በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት
ስእ​ለ​ቴን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ጣ​ለሁ፥
10በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ፥
ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም።
ሃሌ ሉያ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ