መዝ​ሙረ ዳዊት 103:10-13

መዝ​ሙረ ዳዊት 103:10-13 አማ2000

ምን​ጮ​ችን ወደ ቆላ​ዎች የሚ​ልክ፤ በተ​ራ​ሮች መካ​ከል ውኆች ያል​ፋሉ፤ የዱር አራ​ዊ​ትን ሁሉ ያጠ​ጣሉ፥ የበ​ረሃ አህ​ዮ​ችም ጥማ​ታ​ቸ​ውን ያረ​ካሉ። የሰ​ማይ ወፎ​ችም በዚያ ይኖ​ራሉ፤ በዋ​ሻው መካ​ከ​ልም ይጮ​ኻሉ። ተራ​ሮ​ችን ከው​ስ​ጣ​ቸው የሚ​ያ​ጠ​ጣ​ቸው፤ ከሥ​ራህ ፍሬ ምድር ትጠ​ግ​ባ​ለች።