መዝሙር 103:10-13
መዝሙር 103:10-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ምንጮችን ወደ ቆላዎች የሚልክ፤ በተራሮች መካከል ውኆች ያልፋሉ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ያጠጣሉ፥ የበረሃ አህዮችም ጥማታቸውን ያረካሉ። የሰማይ ወፎችም በዚያ ይኖራሉ፤ በዋሻው መካከልም ይጮኻሉ። ተራሮችን ከውስጣቸው የሚያጠጣቸው፤ ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች።
መዝሙር 103:10-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤ እንደ በደላችንም አልከፈለንም። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት። ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣ መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ። አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።