መጽሐፈ መዝሙር 103:10-13

መጽሐፈ መዝሙር 103:10-13 አማ05

በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤ በበደላችንም ልክ አልከፈለንም። ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው። ምሥራቅ ከምዕራብ የሚርቀውን ያኽል እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ከእኛ ያርቀዋል። አባት ለልጆቹ የሚራራላቸውን ያኽል እግዚአብሔርም የሚፈሩትን ይራራላቸዋል።