የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ አብ​ድዩ 1

1
በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ የሚ​ደ​ርስ ቅጣት
1የአ​ብ​ድዩ ራእይ።
ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት። 2እነሆ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ታናሽ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ እጅግ ተን​ቀ​ሃል። 3በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል። 4እንደ ንስር መጥ​ቀህ ብት​ወጣ፥ ቤት​ህም በከ​ዋ​ክ​ብት መካ​ከል ቢሆን፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
5“ሌቦች ቢመ​ጡ​ብህ፥ ወይም ወን​በ​ዴ​ዎች በሌ​ሊት ቢመጡ፥ የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ርቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወይ​ንም የሚ​ቈ​ርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃር​ሚያ አያ​ስ​ቀ​ሩ​ምን? 6ዔሳ​ውን እን​ዴት መረ​መ​ሩት! የሸ​ሸ​ገ​ው​ንም እን​ዴት ወሰ​ዱ​በት! 7የተ​ማ​ማ​ል​ሃ​ቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ዳር​ቻህ ሰደ​ዱህ፤ የተ​ስ​ማ​ሙ​ህም ሰዎች ተነ​ሡ​ብህ፤ አሸ​ነ​ፉ​ህም፤ በበ​ታ​ች​ህም አሽ​ክላ ዘረ​ጉ​ብህ፤ እነ​ር​ሱም ማስ​ተ​ዋል የላ​ቸ​ውም። 8በዚያ ቀን ከኤ​ዶ​ም​ያስ ጥበ​በ​ኞ​ችን፥ ከዔ​ሳው ተራ​ራም ማስ​ተ​ዋ​ልን አጠ​ፋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 9ከዔ​ሳው ተራራ ሰዎች ሁሉ ይጠፉ ዘንድ የቴ​ማን ሰል​ፈ​ኞ​ችህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።
10“በወ​ን​ድ​ምህ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ስለ ተደ​ረገ ኀጢ​አ​ትና ግድያ ኀፍ​ረት ይከ​ድ​ን​ሃል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ትጠ​ፋ​ለህ። 11በፊቱ አን​ጻር በቆ​ምህ ቀን፥ አሕ​ዛብ ጭፍ​ራ​ውን በማ​ረ​ኩ​በት፥ እን​ግ​ዶ​ችም በበሩ በገ​ቡ​በት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዕጣ በተ​ጣ​ጣ​ሉ​በት ቀን አንተ ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ነበ​ርህ። 12በጠ​ላት ቀን ወን​ድ​ም​ህን ዝቅ አድ​ር​ገህ ትመ​ለ​ከ​ተው ዘንድ፥ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭ​ን​ቀ​ታ​ቸ​ውም ቀን በት​ዕ​ቢት ትና​ገር ዘንድ ባል​ተ​ገ​ባህ ነበር። 13በች​ግ​ራ​ቸ​ውም ቀን በሕ​ዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን ጉባ​ኤ​ያ​ቸ​ውን ትመ​ለ​ከት ዘንድ፥ በእ​ል​ቂ​ታ​ቸ​ውም ቀን በሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ላይ አደጋ ትጥል ዘንድ አይ​ገ​ባ​ህም ነበር።#ዕብ. “በሀ​ብ​ታ​ቸው ላይ እጅ​ህን ትዘ​ረጋ ዘንድ ...” ይላል። 14የሸ​ሹ​ት​ንም ለማ​ጥ​ፋት በመ​ተ​ላ​ለ​ፊያ መን​ገ​ዳ​ቸው ትቆም ዘንድ፥ ድል በተ​ነ​ሡ​በ​ትም ቀን ከእ​ርሱ ያመ​ለ​ጡ​ትን ለማ​ስ​ጨ​ነቅ ትከ​ብ​ባ​ቸው ዘንድ ባል​ተ​ገ​ባህ ነበር።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ እን​ደ​ሚ​ፈ​ርድ
15“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ቀር​ቦ​አ​ልና፥ አንተ እንደ አደ​ረ​ግ​ኸው እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ብ​ሃል፤ ፍዳ​ህም በራ​ስህ ላይ ይመ​ለ​ሳል። 16በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ ላይ እንደ ጠጣህ እን​ዲሁ አሕ​ዛብ ሁሉ ወይ​ንን ይጠ​ጣሉ፤ አዎን፥ ይጠ​ጣሉ፥ ይጨ​ል​ጡ​ማል፤ እን​ዳ​ል​ነ​በ​ሩም ይሆ​ናሉ።
የእ​ስ​ራ​ኤል ድል
17“ነገር ግን በጽ​ዮን ተራራ ላይ መድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል፤ እር​ሱም ቅዱስ ይሆ​ናል፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ሰዎች የወ​ረ​ሱ​አ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ግ​ሮ​አ​ልና የያ​ዕ​ቆብ ቤት እሳት፥ የዮ​ሴ​ፍም ቤት ነበ​ል​ባል፥ የዔ​ሳ​ውም ቤት ገለባ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ው​ማል፤ ከዔ​ሳ​ውም ቤት ቅሬታ አይ​ኖ​ርም። 19የደ​ቡ​ብም ሰዎች የዔ​ሳ​ውን ተራራ፥ የቆ​ላ​ውም ሰዎች ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ይወ​ር​ሳሉ፤ የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም ተራራ፥ የሰ​ማ​ር​ያን፥ የብ​ን​ያ​ም​ንና የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ይወ​ር​ሳሉ።#ዕብ. “ብን​ያም ገለ​ዓ​ድን ይወ​ር​ሳል” ይላል። 20ይህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የጭ​ፍ​ራ​ቸው#“የጭ​ፍ​ራ​ቸው” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ምርኮ የከ​ነ​ዓ​ንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራ​ጵታ ድረስ ይወ​ር​ሳል፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምር​ኮ​ኞች እስከ ኤፍ​ራታ ድረስ የደ​ቡ​ብን ከተ​ሞች ይወ​ር​ሳሉ። 21የዳ​ኑ​ትም የዔ​ሳ​ውን ተራራ ይበ​ቀ​ሉት ዘንድ ከጽ​ዮን ተራራ ይዘ​ም​ታሉ፤ መን​ግ​ሥ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ