የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢዩ​ኤል 3

3
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ላይ እን​ደ​ሚ​ፈ​ርድ
1“እነ​ሆም በዚያ ወራ​ትና በዚያ ዘመን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ። 2አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ። 3በሕ​ዝ​ቤም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ፤ ወንድ ልጅን ለአ​መ​ን​ዝ​ሮች ዋጋ ሰጡ፤ ሴት ልጅ​ንም ለወ​ይን ጠጅ ሸጡ፤ ጠጡም።
4“ጢሮ​ስና ሲዶና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም አው​ራጃ ገሊ​ላም ሁሉ ሆይ! ከእ​ና​ንተ ጋራ ምን አለኝ? እና​ንተ በቀ​ልን ትበ​ቀ​ሉ​ኛ​ላ​ች​ሁን? ቂም​ንስ ትቀ​የ​ሙ​ኛ​ላ​ች​ሁን? ፈጥኜ በች​ኰላ ፍዳን በራ​ሳ​ችሁ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ። 5ብሬ​ንና ወር​ቄን ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፥ የተ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም መል​ካ​ሙን ዕቃ​ዬን ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችሁ አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ 6ከዳ​ር​ቻ​ቸ​ውም ታር​ቁ​አ​ቸው ዘንድ የይ​ሁ​ዳን ልጆ​ችና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ልጆች ለግ​ሪክ ልጆች ሸጣ​ች​ኋ​ልና፥ 7እነሆ እነ​ር​ሱን ከሸ​ጣ​ች​ሁ​በት ስፍራ አስ​ነ​ሣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ብድ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም በራ​ሳ​ችሁ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ። 8ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን በይ​ሁዳ ልጆች እጅ እሸ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ለሩ​ቆቹ ሕዝብ#ዕብ. “ለሳባ ሰዎች” ይላል። በም​ርኮ ይሸ​ጡ​አ​ች​ኋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።
9“ይህን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ዐውጁ፤ ለሰ​ልፍ ተዘ​ጋጁ፤ ኀያ​ላ​ንን አስ​ነሡ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይቅ​ረቡ፤ ይው​ጡም። 10ማረ​ሻ​ች​ሁን ሰይፍ፥ ማጭ​ዳ​ች​ሁ​ንም ጦር ለማ​ድ​ረግ ቀጥ​ቅጡ፤ ደካ​ማ​ውም፦ እኔ ብርቱ ነኝ ይበል። 11እና​ንተ በዙ​ሪያ ያላ​ችሁ አሕ​ዛብ ሁሉ፥ ፈጥ​ና​ችሁ ኑ፥ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ የዋ​ሃ​ንም ሰል​ፈ​ኞች ይሁኑ።#ዕብ. “አቤቱ ኀያ​ላ​ኖ​ች​ህን ወደ​ዚያ አው​ርድ” ይላል። 12“አሕ​ዛብ ሁሉ ይነሡ፤ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ሸለ​ቆም ይውጡ፤ በዙ​ሪያ ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ እፈ​ርድ ዘንድ በዚያ እቀ​መ​ጣ​ለ​ሁና። 13መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”
14የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በፍ​ርድ ሸለቆ ቀር​ቦ​አ​ልና ውካ​ታ​ዎች በፍ​ርድ ሸለቆ ተሰሙ። 15ፀሐ​ይና ጨረቃ ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ። 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይጮ​ኻል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ ሰማ​ይና ምድ​ርም ይና​ወ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለሕ​ዝቡ ይራ​ራል፤#ዕብ. “መሸ​ሸ​ጊያ” ይላል። የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ያጸ​ናል።#ዕብ. “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መጠ​ጊያ ይሆ​ናል” ይላል። 17“እኔም በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራዬ በጽ​ዮን የም​ቀ​መጥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​ደ​ሰች ከተማ ትሆ​ና​ለች፥ እን​ግ​ዶ​ችም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ል​ፉ​ባ​ትም።
18“በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ተራ​ሮች ማርን ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ችም ወተ​ትን ያፈ​ስ​ሳሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ያሉት ፈፋ​ዎች ሁሉ ውኃን ያጐ​ር​ፋሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ምንጭ ትፈ​ል​ቃ​ለች፤ የሰ​ኪ​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ታጠ​ጣ​ለች። 19በሀ​ገ​ራ​ቸው ንጹ​ሑን ደም አፍ​ስ​ሰ​ዋ​ልና በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደ​ረ​ጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስም በረሃ ይሆ​ናል። 20ነገር ግን ይሁዳ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለልጅ ልጅ መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች። 21እኔም ደማ​ቸ​ውን እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ አላ​ነ​ጻ​ቸ​ው​ምም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽ​ዮን ያድ​ራል።”#በግ​እ​ዝና በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ምዕ. 3 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 4 ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ