ኦሪት ዘኍ​ልቍ 7:1-10

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 7:1-10 አማ2000

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥ ዐሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ቈ​ጠ​ሩት በላይ የተ​ሾሙ የነ​ገ​ዶች አለ​ቆች ነበሩ። መባ​ቸ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ፤ የተ​ከ​ደኑ ስድ​ስት ሰረ​ገ​ሎች ዐሥራ ሁለ​ትም በሬ​ዎች፤ በየ​ሁ​ለ​ቱም አለ​ቆች አንድ ሰረ​ገላ አቀ​ረቡ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ በሬ በድ​ን​ኳኑ ፊት አቀ​ረቡ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል ይሆን ዘንድ፥ ከእ​ነ​ርሱ ተቀ​ብ​ለህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ስጣ​ቸው።” ሙሴም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን ተቀ​ብሎ ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጣ​ቸው። ለጌ​ድ​ሶን ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሁለት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና አራት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው። ከካ​ህ​ኑም ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ላሉት ለሜ​ራሪ ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው መጠን አራት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስም​ንት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው። ለቀ​ዓት ልጆች ግን መቅ​ደ​ሱን ማገ​ል​ገል የእ​ነ​ርሱ ነውና፥ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ይሸ​ከ​ሙት ነበ​ርና ምንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም። መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።