ኦሪት ዘኍልቍ 24
24
1በለዓምም እስራኤልን መባረክ በእግዚአብሔር ፊት መልካም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ፥ እንደ ልማዱ ለማሟረት ወደ ፊት አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን መለሰ። 2በለዓምም ዐይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዳቸው ሲጓዙ አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ መጣ። 3በምሳሌም ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፥ “የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ በትክክል የሚያይ ሰው እንዲህ ይላል፤
4“የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥
ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥
ተኝቶ ዐይኖቹ የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦
5ያዕቆብ ሆይ፥ ቤቶችህ፥
እስራኤል ሆይ ድንኳኖችህ ምንኛ ያምራሉ!
6እንደሚጋርዱ ዛፎች፥#ዕብ. “ሸለቆች” ይላል።
በወንዝ ዳር እንዳሉ የተክል ቦታዎች፥
እግዚአብሔር እንደ ተከላቸው ድንኳኖች#ዕብ. “እግዚአብሔር እንደ ተከለው እሬት” ይላል።
በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው።
7ከዘሩ ሰው ይወጣል፤
ብዙ ሕዝብንም ይገዛል፥#ዕብ. “ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል ፤ ዘሩም በብዙ ውሆች ይሆናል ፤ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል” ይላል።
መንግሥቱም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ትላለች፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጎግ” ይላል።
መንግሥቱም ትሰፋለች።
8እግዚአብሔር ከግብፅ መርቶ አውጥቶታል፤
አንድ ቀንድ እንዳለው ክብር አለው፤
ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፤
አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፤
በፍላጾቹም ጠላቱን ይወጋዋል።
9አርፎአል፥
እንደ አንበሳና እንደ አንበሳ ደቦል ተጋድሞአል፤
ማን ያስነሣዋል?
የሚመርቁህ ሁሉ የተመረቁ ይሁኑ፤
የሚረግሙህም ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ።”
10ባላቅም በበለዓም ላይ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨበጨበ፤ ባላቅም በለዓምን አለው፦ ጠላቶችን ትረግም ዘንድ ጠራሁህ፥ 11እነሆም፥ ፈጽመህ መረቅሃቸው፤ ይህ ሦስተኛህ ነው፤ አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሂድ፤ እኔ አከብርሃለሁ ብዬ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እነሆ፥ ክብርህን ከለከለ።” 12በለዓምም ባላቅን አለው፦ 13ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ መልካሙን ወይም ክፉውን ከልቤ ለማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤ እግዚአብሔር የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞችህ አልተናገርኋቸውምን? 14አሁንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄዳለሁ፤ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን እነግርሃለሁ።”
የበለዓም የመጨረሻው ትንቢት
15በምሳሌም ይናገር ጀመር፥ እንዲህም አለ፦
“የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥
በትክክል የሚያይ ሰው እንዲህ ይላል፤
16የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥
የልዑልንም ዕውቀት የሚያውቅ፥
ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥
ተኝቶ ዐይኖቹ የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦
17አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤
እባርከዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤
ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፤
ከእስራኤልም ሰው ይነሣል፥#ዕብ. “በትር ይነሣል” ይላል።
የሞዓብንም አለቆች ይመታል፤
የሤትንም ልጆች ሁሉ ይማርካል።
18ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፤
ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤
እስራኤልም በኀይል ያደርጋል።
19ከያዕቆብም ኀያል ሰው ይወጣል፤
ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል።”
20ዐማሌቅንም አይቶ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦
“ዐማሌቅ የአሕዝብ አለቃ ነበረ፤
ዘራቸውም ይጠፋል።”
21ቄኔዎናውያንንም አይቶ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦
“ማደሪያህ የጸናች ናት፤
ጎጆህም በአንባ ላይ ተሠርቶአል፤
22ቢዖር የጥፋት ጎጆ ቢሆንም አሦር ይማርክሃል።”#ዕብ. “ነገር ግን አሦር እስኪማርክህ ቄናዊው ለጥፋት ይሆናል” ይላል።
23አግንም ባየው ጊዜ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦
“እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ
አወይ ማን በሕይወት ይኖራል?
24ከቄጤዎንም እጅ የሚወጣው#ዕብ. “ከኪትም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ” ይላል።
አሦርንና ዕብራውያንን ያስጨንቃል፤
እነርሱም በአንድነት ይጠፋሉ።”#ዕብ. “እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት ይመጣል” ይላል።
25በለዓምም ተነሣ፤ ተመልሶም ወደ ስፍራው ሄደ፤ ባላቅም ደግሞ ወደ ቤቱ ገባ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 24: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ