የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 24

24
1በለ​ዓ​ምም እስ​ራ​ኤ​ልን መባ​ረክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ፥ እንደ ልማዱ ለማ​ሟ​ረት ወደ ፊት አል​ሄ​ደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን መለሰ። 2በለ​ዓ​ምም ዐይ​ኑን አን​ሥቶ እስ​ራ​ኤል በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ሲጓዙ አየ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ መጣ። 3በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የቢ​ዖር ልጅ በለ​ዓም እን​ዲህ ይላል፥ በት​ክ​ክል የሚ​ያይ ሰው እን​ዲህ ይላል፤
4“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥
ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥
ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦
5ያዕ​ቆብ ሆይ፥ ቤቶ​ችህ፥
እስ​ራ​ኤል ሆይ ድን​ኳ​ኖ​ችህ ምንኛ ያም​ራሉ!
6እን​ደ​ሚ​ጋ​ርዱ ዛፎች፥#ዕብ. “ሸለ​ቆች” ይላል።
በወ​ንዝ ዳር እን​ዳሉ የተ​ክል ቦታ​ዎች፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተከ​ላ​ቸው ድን​ኳ​ኖች#ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተከ​ለው እሬት” ይላል።
በው​ኃም ዳር እን​ዳሉ ዝግ​ባ​ዎች ናቸው።
7ከዘሩ ሰው ይወ​ጣል፤
ብዙ ሕዝ​ብ​ንም ይገ​ዛል፥#ዕብ. “ከማ​ድ​ጋ​ዎቹ ውኃ ይፈ​ስ​ሳል ፤ ዘሩም በብዙ ውሆች ይሆ​ናል ፤ ንጉ​ሡም ከአ​ጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል” ይላል።
መን​ግ​ሥ​ቱም ከአ​ጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ትላ​ለች፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጎግ” ይላል።
መን​ግ​ሥ​ቱም ትሰ​ፋ​ለች።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ መርቶ አው​ጥ​ቶ​ታል፤
አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር አለው፤
ጠላ​ቶ​ቹን አሕ​ዛ​ብን ይበ​ላል፤
አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ባ​ብ​ራል፤
በፍ​ላ​ጾ​ቹም ጠላ​ቱን ይወ​ጋ​ዋል።
9አር​ፎ​አል፥
እንደ አን​በ​ሳና እንደ አን​በሳ ደቦል ተጋ​ድ​ሞ​አል፤
ማን ያስ​ነ​ሣ​ዋል?
የሚ​መ​ር​ቁህ ሁሉ የተ​መ​ረቁ ይሁኑ፤
የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህም ሁሉ የተ​ረ​ገሙ ይሁኑ።”
10ባላ​ቅም በበ​ለ​ዓም ላይ ተቈጣ፤ እጆ​ቹ​ንም አጨ​በ​ጨበ፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፦ ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግም ዘንድ ጠራ​ሁህ፥ 11እነ​ሆም፥ ፈጽ​መህ መረ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ይህ ሦስ​ተ​ኛህ ነው፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ወደ ስፍ​ራህ ሂድ፤ እኔ አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ ብዬ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እነሆ፥ ክብ​ር​ህን ከለ​ከለ።” 12በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን አለው፦ 13ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ብርና ወርቅ ቢሰ​ጠኝ፥ መል​ካ​ሙን ወይም ክፉ​ውን ከልቤ ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላ​ክ​ሃ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ው​ምን? 14አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋ​ለ​ኛው ዘመን በሕ​ዝ​ብህ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።”
የበ​ለ​ዓም የመ​ጨ​ረ​ሻው ትን​ቢት
15በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፥ እን​ዲ​ህም አለ፦
“የቢ​ዖር ልጅ በለ​ዓም እን​ዲህ ይላል፥
በት​ክ​ክል የሚ​ያይ ሰው እን​ዲህ ይላል፤
16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥
የል​ዑ​ል​ንም ዕው​ቀት የሚ​ያ​ውቅ፥
ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥
ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦
17አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤
እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤
ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤
ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥#ዕብ. “በትር ይነ​ሣል” ይላል።
የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤
የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።
18ኤዶ​ም​ያ​ስም ርስቱ ይሆ​ናል፤
ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆ​ናል፤
እስ​ራ​ኤ​ልም በኀ​ይል ያደ​ር​ጋል።
19ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀያል ሰው ይወ​ጣል፤
ከከ​ተ​ማ​ውም የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋል።”
20ዐማ​ሌ​ቅ​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦
“ዐማ​ሌቅ የአ​ሕ​ዝብ አለቃ ነበረ፤
ዘራ​ቸ​ውም ይጠ​ፋል።”
21ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦
“ማደ​ሪ​ያህ የጸ​ናች ናት፤
ጎጆ​ህም በአ​ንባ ላይ ተሠ​ር​ቶ​አል፤
22ቢዖር የጥ​ፋት ጎጆ ቢሆ​ንም አሦር ይማ​ር​ክ​ሃል።”#ዕብ. “ነገር ግን አሦር እስ​ኪ​ማ​ር​ክህ ቄና​ዊው ለጥ​ፋት ይሆ​ናል” ይላል።
23አግ​ንም ባየው ጊዜ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦
“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሲያ​ደ​ርግ
አወይ ማን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል?
24ከቄ​ጤ​ዎ​ንም እጅ የሚ​ወ​ጣው#ዕብ. “ከኪ​ትም ዳርቻ መር​ከ​ቦች ይመ​ጣሉ” ይላል።
አሦ​ር​ንና ዕብ​ራ​ው​ያ​ንን ያስ​ጨ​ን​ቃል፤
እነ​ር​ሱም በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ።”#ዕብ. “እር​ሱም ደግሞ ወደ ጥፋት ይመ​ጣል” ይላል።
25በለ​ዓ​ምም ተነሣ፤ ተመ​ል​ሶም ወደ ስፍ​ራው ሄደ፤ ባላ​ቅም ደግሞ ወደ ቤቱ ገባ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ