የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 11

11
የቃ​ጠ​ሎው ቦታ
1ሕዝ​ቡም በክ​ፋት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ነደ​ደች፤ ከሰ​ፈ​ሩም አን​ዱን ወገን በላች። 2ሕዝ​ቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እሳ​ቲ​ቱም ጠፋች። 3ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ እሳት ስለ ነደ​ደች የዚያ ስፍራ ስም “መካነ ውዕ​የት”#ዕብ. “ተቤራ” ይላል። ተብሎ ተጠራ።
ለእ​ስ​ራ​ኤል ከሰ​ማይ መና እንደ ወረ​ደ​ላ​ቸው
4ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቀ​ም​ጠው እን​ዲህ እያሉ አለ​ቀሱ፥ “ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል? 5በግ​ብፅ ያለ ዋጋ እን​በ​ላው የነ​በ​ረ​ውን ዓሣ፥ ዳቦ​ው​ንም፥ በጢ​ኹ​ንም፥ ኩራ​ቱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ሽን​ኩ​ርት፥ ነጩ​ንም ሽን​ኩ​ርት ቍንዶ በር​በ​ሬ​ው​ንም እና​ስ​ባ​ለን። 6አሁን ግን ሰው​ነ​ታ​ችን ደረ​ቀች፤ ዐይ​ና​ች​ንም ከዚህ መና በቀር ምንም አታ​ይም” አሉ። 7መና​ውም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነበረ፤ መል​ኩም እንደ በረድ ነጭ ነበር። 8ሕዝ​ቡም እየ​ዞሩ ይለ​ቅሙ ነበር፤ በወ​ፍ​ጮም ይፈ​ጩት፥ ወይም በሙ​ቀጫ ይወ​ቅ​ጡት፥ በም​ን​ቸ​ትም ይቀ​ቅ​ሉት ነበር፤ እን​ጎ​ቻም ያደ​ር​ጉት ነበር፤ ጣዕ​ሙም በዘ​ይት እንደ ተለ​ወሰ እን​ጎቻ ነበረ። 9ሌሊ​ትም ጠል በሰ​ፈሩ ላይ በወ​ረደ ጊዜ መናው በላዩ ይወ​ርድ ነበር።
10ሙሴም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ፥ ሲያ​ለ​ቅሱ ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ተቈጣ፤ ነገ​ሩም በሙሴ ፊት ክፉ ሆነ። 11ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ላይ ክፉ አደ​ረ​ግህ? ለም​ንስ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አላ​ገ​ኘ​ሁም? ለም​ንስ የዚ​ህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደ​ረ​ግህ? 12አንተ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ህ​ላ​ቸው ምድር አደ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ፦ ሞግ​ዚት የሚ​ጠ​ባ​ውን ልጅ እን​ድ​ታ​ቅፍ በብ​ትህ እቀ​ፋ​ቸው የም​ት​ለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነ​ስ​ሁ​ትን? ወይስ ወለ​ድ​ሁ​ትን? 13በፊቴ ያለ​ቅ​ሳ​ሉና፦ የም​ን​በ​ላ​ውን ሥጋ ስጠን ይላ​ሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የም​ሰ​ጠው ሥጋ ከየት አለኝ? 14እጅግ ከብ​ዶ​ኛ​ልና ይህን ሁሉ ሕዝብ ብቻ​ዬን ልሸ​ከም አል​ች​ልም። 15እን​ዲ​ህስ ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ፥ በፊ​ትህ ይቅ​ር​ታን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ፥ እባ​ክህ፥ ፈጽሞ ግደ​ለኝ።”
የሰ​ብ​ዓው ሊቃ​ናት መመ​ረጥ
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ለሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ጸሐ​ፍት ይሆኑ ዘንድ የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብ​ስ​ብ​ልኝ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን አም​ጣ​ቸው፤ በዚ​ያም ከአ​ንተ ጋር አቁ​ማ​ቸው። 17እኔም እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ያም አነ​ጋ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ በአ​ንተ ካለ​ውም መን​ፈስ ወስጄ በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ብቻ እን​ዳ​ት​ሸ​ከም የሕ​ዝ​ቡን ሸክም ከአ​ንተ ጋር ይሸ​ከ​ማሉ። 18ሕዝ​ቡ​ንም በላ​ቸው፦ ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል? በግ​ብፅ ደኅና ነበ​ረ​ልን እያ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና ለነገ ተቀ​ደሱ፤ ሥጋ​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሥጋን ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ትበ​ሉ​ማ​ላ​ችሁ። 19አንድ ቀን፥ ወይም ሁለት ቀን፥ ወይም አም​ስት ቀን፥ ወይም ዐሥር ቀን ወይም ሃያ ቀን አት​በ​ሉም፤ 20ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያለ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ች​ኋ​ልና፥ በፊ​ቱም፦ ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን? ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና በአ​ፍ​ን​ጫ​ችሁ እስ​ኪ​ወጣ መር​ዝም እስ​ኪ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።” 21ሙሴም፥ “እኔ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያለሁ ሕዝብ ስድ​ስት መቶ ሺህ እግ​ረኛ ናቸው፤ አን​ተም፦ ሥጋን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ወር ሙሉም ይበ​ሉ​ታል አልህ። 22የበ​ሬና የበግ መንጋ ቢታ​ረድ፥ የባ​ሕር ዓሣ ሁሉ ቢሰ​በ​ሰብ ይበ​ቃ​ቸ​ዋ​ልን?” አለ። 23እግ​ዚ​አ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አት​ች​ል​ምን? አሁን ቃሌ ይፈ​ጸም ወይም አይ​ፈ​ጸም እንደ ሆነ እነሆ፥ አንተ ታያ​ለህ” አለው።
24ሙሴም ወጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃሎች ለሕ​ዝቡ ነገረ፤ ከሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሰባ​ውን ሰዎች ሰብ​ስቦ በድ​ን​ኳኑ ዙሪያ አቆ​ማ​ቸው። 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ወረደ፤ ተና​ገ​ረ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ላይ ከነ​በ​ረው መን​ፈስ ወስዶ በሰ​ባው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ላይ አደ​ረገ፤ መን​ፈ​ሱም በላ​ያ​ቸው ባደረ ጊዜ ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አል​ተ​ጨ​መ​ረ​ላ​ቸ​ውም።
26ከእ​ነ​ር​ሱም ሁለት ሰዎች በሰ​ፈር ቀር​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ስም ኤል​ዳድ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ሞዳድ ነበረ፤ መን​ፈ​ስም ዐረ​ፈ​ባ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ከተ​ጻ​ፉት ጋር ነበሩ፤ ወደ ድን​ኳኑ ግን አል​ወ​ጡም ነበር፤ በሰ​ፈ​ሩም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገሩ። 27አንድ ጐል​ማሳ ሰው እየ​ሮጠ መጥቶ፥ “ኤል​ዳ​ድና ሞዳድ በሰ​ፈር ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ” ብሎ ለሙሴ ነገ​ረው። 28የሙሴ ምርጥ ባለ​ሟል የነ​በ​ረው የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ ፥ ከል​ክ​ላ​ቸው” አለው። 29ሙሴም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሱን ቢያ​ሳ​ድር አንተ ስለ እኔ ትቀ​ና​ለ​ህን?” አለው። 30ሙሴም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጋር ወደ ሰፈር ተመ​ለሰ።
ድር​ጭት እንደ ወረ​ደ​ላ​ቸው
31ነፋ​ስም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ ከባ​ሕ​ርም ድር​ጭ​ቶ​ችን አወጣ፤ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚህ፥ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚያ በሰ​ፈሩ ላይ በተ​ና​ቸው፤ በዚ​ያም በሰ​ፈሩ ዙሪያ ከፍ​ታው ከም​ድር ወደ ላይ ሁለት ክንድ ነበረ። 32በዚ​ያም ቀን ሁሉ፥ በሌ​ሊ​ትም ሁሉ፥ በነ​ጋ​ውም ሁሉ ሕዝቡ ተነ​ሥ​ተው ድር​ጭ​ትን ሰበ​ሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰ​በ​ሰበ ዐሥር የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ያህል ሰበ​ሰበ፤ በሰ​ፈ​ሩም ዙሪያ ሁሉ አስ​ጥ​ተው አደ​ረ​ቁት። 33ሥጋ​ውም ገና በጥ​ር​ሳ​ቸው መካ​ከል ሳለ ሳያ​ኝ​ኩ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅ​ሠ​ፍት አጠ​ፋ​ቸው። 34የጐ​መጁ ሕዝብ በዚያ ተቀ​ብ​ረ​ዋ​ልና የዚያ ስፍራ ስም “መቃ​ብረ ፍት​ወት” ተብሎ ተጠራ። 35ሕዝ​ቡም ከመ​ቃ​ብረ ፍት​ወት ወደ አሴ​ሮት ተጓዙ፤ በአ​ሴ​ሮ​ትም ተቀ​መጡ።#በግ​እዙ ምዕ. 11 በቍ. 34 ያበ​ቃል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}