የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 10

10
የብር መለ​ከ​ቶች
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ሁለት የብር መለ​ከ​ቶች አስ​ጠ​ፍ​ጥ​ፈህ ለአ​ንተ አድ​ርግ፤ ማኅ​በ​ሩን ለመ​ጥ​ራት ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም ለማ​ስ​ጓዝ ይሁ​ኑ​ልህ። 3ሁለ​ቱም መለ​ከ​ቶች በተ​ነፉ ጊዜ ማኅ​በሩ ሁሉ#በዕብ. “ወደ አንተ” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። ወደ አንተ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይሰ​ብ​ሰቡ። 4አንድ መለ​ከት ሲነፋ ታላ​ላ​ቆቹ የእ​ስ​ራ​ኤል አእ​ላፍ አለ​ቆች ወደ አንተ ይሰ​ብ​ሰቡ። 5መለ​ከ​ቱ​ንም በም​ል​ክት ስት​ነፉ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ። 6ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ ስት​ነፉ በአ​ዜብ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ በነ​ፋ​ችሁ ጊዜ በባ​ሕር በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ፤ አራ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ በነ​ፋ​ችሁ ጊዜ በመ​ስዕ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ሠራ​ዊት ይጓዙ፤ ለማ​ስ​ጓዝ በም​ል​ክት ትነ​ፉ​ታ​ላ​ችሁ። 7ጉባ​ኤ​ውም በሚ​ሰ​በ​ሰ​ብ​በት ጊዜ ያለ ምል​ክት ትነ​ፉ​ታ​ላ​ችሁ። 8የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ መለ​ከ​ቱን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ። 9በሚ​ገ​ፋ​ች​ሁም ጠላት ላይ በም​ድ​ራ​ችሁ ወደ ሰልፍ ስት​ወጡ በም​ል​ክት መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ትታ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ትድ​ና​ላ​ችሁ። 10ደግሞ በደ​ስ​ታ​ችሁ ቀን፥ በበ​ዓ​ላ​ታ​ች​ሁም ዘመን፥ በወ​ርም መባቻ፥ በሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁና በደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ላይ መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ እነ​ር​ሱም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”
እስ​ራ​ኤል ከሲና እንደ ተነሡ
11በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ደመ​ናው ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ላይ ተነሣ። 12የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየ​ጉ​ዞ​አ​ቸው ተጓዙ፤ ደመ​ና​ውም በፋ​ራን ምድረ በዳ ቆመ። 13በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እን​ዳ​ዘዘ ተጓዙ። 14በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም የይ​ሁዳ ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን አለቃ ነበረ። 15በይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል አለቃ ነበረ። 16በዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ አለቃ ነበረ።
17ድን​ኳ​ኑም ተነ​ቀለ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም የተ​ሸ​ከሙ የጌ​ድ​ሶን ልጆ​ችና የሜ​ራሪ ልጆች ተጓዙ። 18የሮ​ቤ​ልም ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የሰ​ዲ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር አለቃ ነበረ። 19በስ​ም​ዖ​ንም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል አለቃ ነበረ። 20በጋ​ድም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤሊ​ሳፍ አለቃ ነበረ።
21የቀ​ዓ​ትም ልጆች ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን ተሸ​ክ​መው ተጓዙ፤ እነ​ዚ​ህም እስ​ኪ​መጡ ድረስ እነ​ዚያ ድን​ኳ​ኑን ተከሉ። 22የኤ​ፍ​ሬ​ምም ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የኣ​ሚ​ሁድ ልጅ ኤሊ​ሳማ አለቃ ነበረ። 23በም​ና​ሴም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል አለቃ ነበረ። 24በብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የጋ​ዲ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን አለቃ ነበረ። 25ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር አለቃ ነበረ። 26በአ​ሴ​ርም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋግ​ኤል አለቃ ነበረ። 27በን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የዔ​ናን ልጅ አኪሬ አለቃ ነበረ። 28የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጉዞ እን​ደ​ዚህ ነበር፤ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዙ።
29ሙሴም የሚ​ስ​ቱን አባት የም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ውን የራ​ጉ​ኤ​ልን ልጅ ኦባ​ብን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ለእ​ና​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ ወዳ​ለው ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል መል​ካ​ምን ነገር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መል​ካ​ምን እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አለው። 30እር​ሱም፥ “አል​ሄ​ድም፥ ነገር ግን ወደ ሀገ​ሬና ወደ ዘመ​ዶች እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው። 31እር​ሱም፥ “እባ​ክህ፥ በም​ድረ በዳ#ዕብ. “ የም​ን​ሰ​ፍ​ር​በ​ትን አንተ ታው​ቃ​ለ​ህና እንደ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ንም ትሆ​ን​ል​ና​ለ​ህና” ይላል። ከእኛ ጋር ኑረ​ሃ​ልና በእ​ኛም ዘንድ አር​ጅ​ተ​ሃ​ልና አት​ተ​ወን፤ 32ከእ​ኛም ጋር ብት​ሄድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ልን መል​ካም ነገር ሁሉ እኛ ለአ​ንተ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አለው።
ሕዝቡ ጉዞ እንደ ጀመሩ
33ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ተጓዙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኪ​ዳኑ ታቦት#ዕብ. “የሚ​ያ​ድ​ር​በ​ትን ስፍራ ይፈ​ል​ግ​ላ​ቸው ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ቀደ​ማ​ቸው” ይላል። የሚ​ያ​ድ​ሩ​በ​ትን ቦታ ታገ​ኝ​ላ​ቸው ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ትቀ​ድ​ማ​ቸው ነበር።
34ሙሴም ታቦቷ በተ​ጓ​ዘች ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ተነሣ፤ ጠላ​ቶ​ችህ ይበ​ተኑ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ህም ከፊ​ትህ ይሽሹ” ይል ነበር። 35ባረ​ፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስ​ራ​ኤል እልፍ አእ​ላ​ፋት ተመ​ለስ” ይል ነበር።
36ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም በተ​ጓዙ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደመና ቀን ቀን በላ​ያ​ቸው ላይ ነበረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ