መጽሐፈ ነህምያ 4
4
ነህምያ ጠላቶቹን እንደ ተቋቋመ
1ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበሳጨም፤ በአይሁድም ሳቀባቸው። 2በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፥ “ከተማቸውን የሚሠሩ እነዚህ ደካሞች#“ደካሞች” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አይሁድ ኀይላቸው ምንድን ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን?” ብሎ ተናገረ። 3አሞናዊውም ጦቢያ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “በድንጋይ በሚሠሩት ቅጥራቸው ላይ ቀበሮ ቢወጣበት ያፈርሰዋል” አለ። 4አምላካችን ሆይ፥ ተንቀናልና ስማ፤ ስድባቸውን በራሳቸው ላይ መልስባቸው፤ በምርኮ ሀገር ለብዝበዛ አሳልፈህ ስጣቸው። 5በደላቸውንም አትክደን፤ ኀጢአታቸውም ከፊትህ አይደምሰስ፤ በሠራተኞች ፊት አስቈጥተውሃልና። 6ቅጥሩንም ሠራን፤ ቅጥሩም ሁሉ እስከ እኩሌታው ድረስ ተጋጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበርና።#ምዕ. 4 ቍ. 6 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
7ሰንባላጥና ጦብያም፥ ዓረባውያንም፥ አሞናውያንም፥ አዛጦናውያንም#“አዛጦናውያንም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የኢየሩሳሌም ቅጥር እየታደሰ እንደ ሄደ፥ የፈረሰውም ሊጠገን እንደ ተጀመረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ። 8መጥተውም ኢየሩሳሌምን ይወጉና ያፈርሷት ዘንድ ሁሉም በአንድነት ተሰበሰቡ። 9እኛም ወደ አምላካችን ጸለይን፤ ከእነርሱም የተነሣ በአንጻራቸው ተጠባባቂዎችን በሌሊትና በቀን አደረግን። 10ይሁዳም፥ “የተሸካሚዎች ኀይል ደከመ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጠላቶች ኀይል ደከመ” ይላል። ፍርስራሹም ብዙ ነው፤ ቅጥሩንም እንሠራ ዘንድ አንችልም” አሉ። 11ጠላቶቻችንም፥ “ወደ መካከላቸው እስክንመጣና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጕል ድረስ አያውቁም፤ አያዩም” አሉ። 12በአጠገባቸውም የተቀመጡት አይሁድ መጥተው፥ “ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል ብለው ዐሥር ጊዜ ነገሩን።” 13ከቅጥሩም በስተኋላ በኩል ባለው በታችኛው ክፍል በሰዋራ ስፍራ ሰይፋቸውንና ጦራቸውን፥ ቀስታቸውንም አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኋቸው፤ 14አይችም ተነሣሁ፤ ታላላቆቹንና ሹሞቹንም፥ የቀሩትንም ሕዝብ፥ “አትፍሩአቸው፤ ታላቁንና የተፈራውን አምላካችንን አስቡ፤ ስለ ወንድሞቻችሁም፥ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ስለ ሚስቶቻችሁም፥ ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ” አልኋቸው።
15ጠላቶቻችንም እንደ ዐወቅንባቸው፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው ሰሙ፤ እኛም ሁላችን ወደ ቅጥሩ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን። 16ከዚያም ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ብላቴኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩሌቶቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስትና ጥሩርም ይዘው በፊትና በኋላ ይጠብቁ#በፊትና በኋላ ይጠብቁ” የሚለው በግእዝ ብቻ። ነበር፤ አለቆቹም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር። 17ቅጥሩንም የሚሠሩትና ሸክም ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ ነበር፤ በአንድ እጃቸውም የጦር መሣሪያቸውን ይይዙ ነበር። 18አናጢዎቹም ሁሉ እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ ቀንደ መለከትም የሚነፋ በአጠገቤ ነበረ። 19ታላላቆቹንና ሹሞቹን፥ የቀሩትንም ሕዝብ፥ “ሥራው ታላቅና ሰፊ ነው፤ እኛም በቅጥሩ ላይ ተበታትነናል፤ አንዱም ከሁለተኛው ርቆአል፤ 20የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል” አልኋቸው።
21ሥራውንም እንሠራ ነበር፤ ከማለዳ ወገግታም ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ እኩሌቶቹ ጦር ይይዙ ነበር። 22ደግሞም በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፥ “ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር#“ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በኢየሩሳሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌሊትም ጠባቂዎች ሁኑልን፤ በቀንም ሥሩ” አልኋቸው። 23እኔና ወንድሞችም፥ ብላቴኖችም#“ወንድሞችም ብላቴኖችም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በኋላዬም የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። ወደ ውኃም ስንሄድ መሣሪያችንን እንደታጠቅን እንሄድ ነበር።#“ወደ ውኃው ስንሄድ መሣሪያችንን እንደታጠቅን እንሄድ ነበር” የሚለው በግእዝ ብቻ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 4: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ