የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 4

4
ነህ​ምያ ጠላ​ቶ​ቹን እንደ ተቋ​ቋመ
1ሰን​ባ​ላ​ጥም ቅጥ​ሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበ​ሳ​ጨም፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ሳቀ​ባ​ቸው። 2በወ​ን​ድ​ሞ​ቹና በሰ​ማ​ርያ ሠራ​ዊ​ትም ፊት፥ “ከተ​ማ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ እነ​ዚህ ደካ​ሞች#“ደካ​ሞች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አይ​ሁድ ኀይ​ላ​ቸው ምን​ድን ነው? ይተ​ዉ​ላ​ቸ​ዋ​ልን? ይሠ​ዋ​ሉን? በአ​ንድ ቀንስ ይጨ​ር​ሳ​ሉን? የተ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንስ ድን​ጋይ ከፍ​ር​ስ​ራሹ መል​ሰው ያድ​ኑ​ታ​ልን?” ብሎ ተና​ገረ። 3አሞ​ና​ዊ​ውም ጦቢያ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “በድ​ን​ጋይ በሚ​ሠ​ሩት ቅጥ​ራ​ቸው ላይ ቀበሮ ቢወ​ጣ​በት ያፈ​ር​ሰ​ዋል” አለ። 4አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተን​ቀ​ና​ልና ስማ፤ ስድ​ባ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መል​ስ​ባ​ቸው፤ በም​ርኮ ሀገር ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው። 5በደ​ላ​ቸ​ው​ንም አት​ክ​ደን፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከፊ​ትህ አይ​ደ​ም​ሰስ፤ በሠ​ራ​ተ​ኞች ፊት አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ሃ​ልና። 6ቅጥ​ሩ​ንም ሠራን፤ ቅጥ​ሩም ሁሉ እስከ እኩ​ሌ​ታው ድረስ ተጋ​ጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበ​ርና።#ምዕ. 4 ቍ. 6 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
7ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦብ​ያም፥ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አሞ​ና​ው​ያ​ንም፥ አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም#“አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጥር እየ​ታ​ደሰ እንደ ሄደ፥ የፈ​ረ​ሰ​ውም ሊጠ​ገን እንደ ተጀ​መረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ። 8መጥ​ተ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይወ​ጉና ያፈ​ር​ሷት ዘንድ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ። 9እኛም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ጸለ​ይን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ነሣ በአ​ን​ጻ​ራ​ቸው ተጠ​ባ​ባ​ቂ​ዎ​ችን በሌ​ሊ​ትና በቀን አደ​ረ​ግን። 10ይሁ​ዳም፥ “የተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎች ኀይል ደከመ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጠ​ላ​ቶች ኀይል ደከመ” ይላል። ፍር​ስ​ራ​ሹም ብዙ ነው፤ ቅጥ​ሩ​ንም እን​ሠራ ዘንድ አን​ች​ልም” አሉ። 11ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ “ወደ መካ​ከ​ላ​ቸው እስ​ክ​ን​መ​ጣና እስ​ክ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው ድረስ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም እስ​ክ​ና​ስ​ተ​ጓ​ጕል ድረስ አያ​ው​ቁም፤ አያ​ዩም” አሉ። 12በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት አይ​ሁድ መጥ​ተው፥ “ከስ​ፍ​ራው ሁሉ ይመ​ጡ​ብ​ናል ብለው ዐሥር ጊዜ ነገ​ሩን።” 13ከቅ​ጥ​ሩም በስ​ተ​ኋላ በኩል ባለው በታ​ች​ኛው ክፍል በሰ​ዋራ ስፍራ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንና ጦራ​ቸ​ውን፥ ቀስ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ይዤ ሕዝ​ቡን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቆ​ም​ኋ​ቸው፤ 14አይ​ችም ተነ​ሣሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ፥ “አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ታላ​ቁ​ንና የተ​ፈ​ራ​ውን አም​ላ​ካ​ች​ንን አስቡ፤ ስለ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ቤቶ​ቻ​ች​ሁም ተዋጉ” አል​ኋ​ቸው።
15ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እንደ ዐወ​ቅ​ን​ባ​ቸው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምክ​ራ​ቸ​ውን ከንቱ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሰሙ፤ እኛም ሁላ​ችን ወደ ቅጥሩ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ወደ ሥራ​ችን ተመ​ለ​ስን። 16ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እኩ​ሌ​ቶቹ ብላ​ቴ​ኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስ​ትና ጥሩ​ርም ይዘው በፊ​ትና በኋላ ይጠ​ብቁ#በፊ​ትና በኋላ ይጠ​ብቁ” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር። 17ቅጥ​ሩ​ንም የሚ​ሠ​ሩ​ትና ሸክም ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ በአ​ንድ እጃ​ቸው ይሠሩ ነበር፤ በአ​ንድ እጃ​ቸ​ውም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይይዙ ነበር። 18አና​ጢ​ዎ​ቹም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰይ​ፉን በወ​ገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ ቀንደ መለ​ከ​ትም የሚ​ነፋ በአ​ጠ​ገቤ ነበረ። 19ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ፥ “ሥራው ታላ​ቅና ሰፊ ነው፤ እኛም በቅ​ጥሩ ላይ ተበ​ታ​ት​ነ​ናል፤ አን​ዱም ከሁ​ለ​ተ​ኛው ርቆ​አል፤ 20የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ ወደ​ም​ት​ሰ​ሙ​በት ስፍራ ወደ​ዚያ ወደ እኛ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ አም​ላ​ካ​ችን ስለ እኛ ይዋ​ጋል” አል​ኋ​ቸው።
21ሥራ​ው​ንም እን​ሠራ ነበር፤ ከማ​ለዳ ወገ​ግ​ታም ጀምሮ ከዋ​ክ​ብት እስ​ኪ​ወጡ ድረስ እኩ​ሌ​ቶቹ ጦር ይይዙ ነበር። 22ደግ​ሞም በዚያ ጊዜ ሕዝ​ቡን፥ “ሁላ​ችሁ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቻ​ችሁ ጋር#“ሁላ​ችሁ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቻ​ችሁ ጋር” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ጠባ​ቂ​ዎች ሁኑ​ልን፤ በቀ​ንም ሥሩ” አል​ኋ​ቸው። 23እኔና ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም#“ወን​ድ​ሞ​ችም ብላ​ቴ​ኖ​ችም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በኋ​ላ​ዬም የነ​በ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች ልብ​ሳ​ች​ንን አና​ወ​ል​ቅም ነበር። ወደ ውኃም ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር።#“ወደ ውኃው ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ