የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 3

3
1ታላ​ቁም ካህን ኤል​ያ​ሴ​ብና ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናት ተነ​ሥ​ተው የበግ በር ሠሩ፤ ቀደ​ሱ​ትም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ እስከ መቶ ግን​ብና እስከ ሐና​ን​ኤል ግንብ ድረስ ቀደ​ሱት። 2በአ​ጠ​ገ​ቡም የኢ​ያ​ሪኮ ሰዎች ሠሩ፤ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የአ​ምሪ ልጅ የዘ​ኩር ልጆች ሠሩ።
3የአ​ስ​ናሃ ልጆ​ችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ። 4በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የሜ​ሴ​ዜ​ቤል ልጅ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የበ​ሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ። 5በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ቴቁ​ሓ​ው​ያን ይሠሩ ጀመሩ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸው ግን ለሥ​ራው አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አላ​ዋ​ረ​ዱም።
6የፋ​ሴሓ ልጅ ኢዮ​ዳ​ሄና የበ​ሶ​ድያ ልጅ ሜሱ​ላም አሮ​ጌ​ውን#ግእዝ “ያስ​ናይ” ይላል አሮጌ ማለት ነው። በር አደሱ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹን አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ። 7በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ገባ​ዖ​ና​ዊው መል​ጥ​ያና ሜሮ​ና​ታ​ዊው ያዴን፥ እስከ ወን​ዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑ የገ​ባ​ዖ​ንና የመ​ሴፋ ሰዎች ሠሩ። 8በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኛው የሐ​ሬ​ህያ ልጅ ዑዝ​ኤል ሠራ። በአ​ጠ​ገ​ቡም ከሽቱ ቀማ​ሚ​ዎች የነ​በረ ሐና​ንያ ሠራ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ጠገኑ። 9በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ ሠራ። 10በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኤ​ር​ማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ። በአ​ጠ​ገ​ቡም የአ​ሰ​ብ​ን​ብ​ሔም ልጅ ሐጡስ ሠራ። 11የካ​ሪም ልጅ መል​ክያ፥ የፈ​ሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላ​ውን ክፍ​ልና#“ሌላ​ውን ክፍ​ልና” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። የእ​ቶ​ኑን ግንብ ሠሩ። 12በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የአ​ሎ​ኤስ ልጅ ሰሎ​ምና ሴቶች ልጆቹ ሠሩ።
13ሐኖ​ንና የዘ​ናን ሰዎ​ችም የሸ​ለ​ቆ​ውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ፤ ደግ​ሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚ​ሆን ቅጥር ሠሩ።
14የቤ​ት​ሐ​ካ​ሪ​ምም ግዛት ገዢ የሬ​ካብ ልጅ መል​ክያ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ከል​ጆቹ ጋር#“ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ከል​ጆቹ ጋር” የሚ​ለው በዕብ. የለም። የጕ​ድፍ መጣ​ያ​ውን በር ሠራ፤ ከደ​ነው፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ።
15የመ​ሴ​ፋም ገዢ የኮ​ል​ሐዜ ልጅ ሰሎም የም​ን​ጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደ​ነ​ውም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ከዳ​ዊ​ትም ከተማ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው ደረጃ ድረስ በን​ጉሡ አት​ክ​ልት አጠ​ገብ ያለ​ውን የመ​ዋኛ ቅጥር ሠራ። 16ከእ​ር​ሱም በኋላ የቤ​ሶር ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የዓ​ዛ​ቡህ ልጅ ነህ​ምያ በዳ​ዊት መቃ​ብር አን​ጻር እስ​ካ​ለው ስፍራ፥ እስከ ተሠ​ራ​ውም መዋኛ፥ እስከ ኀያ​ላ​ኑም ቤት ድረስ ሠራ። 17ከእ​ር​ሱም በኋላ ሌዋ​ው​ያ​ንና የባኒ ልጅ ሬሁም ሠሩ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቅ​ዒላ ግዛት እኩ​ሌ​ታና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ገዢ አሰ​ብያ ሠራ። 18ከእ​ር​ሱም በኋላ የቅ​ዔላ ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የኤ​ን​ሐ​ዳድ ልጅ ቤኒ​ይና ወን​ድ​ሞቹ ሠሩ። 19በአ​ጠ​ገ​ቡም የመ​ሴፋ ገዢ የኢ​ያሱ ልጅ አዙር በማ​ዕ​ዘኑ አጠ​ገብ በመ​ወ​ጣ​ጫው ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ። 20ከእ​ር​ሱም በኋላ የዘ​ቡር ልጅ ባሮክ ከማ​ዕ​ዘኑ ጀምሮ እስከ ታላቁ ካህን እስከ ኤል​ያ​ሴብ ቤት መግ​ቢያ ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ተግቶ ሠራ። 21ከእ​ር​ሱም በኋላ የአ​ቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ከኤ​ል​ያ​ሴብ ቤት መግ​ቢያ ጀምሮ እሰከ ኤል​ያ​ሴብ ቤት መጨ​ረሻ ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ሠራ። 22ከእ​ር​ሱም በኋላ የአ​ካ​ባ​ቢው ሰዎች ካህ​ናቱ ሠሩ። 23ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ብን​ያ​ምና አሴብ በቤ​ታ​ቸው አን​ጻር ያለ​ውን ሠሩ። ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የሐ​ና​ንያ ልጅ የመ​ዓ​ስያ ልጅ ዓዛ​ር​ያስ በቤቱ አጠ​ገብ ያለ​ውን ሠራ። 24ከእ​ር​ሱም በኋላ የኢ​ን​ሓ​ዳድ ልጅ ባኒ ከዓ​ዛ​ር​ያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ እስከ ግን​ቡ​መ​ዞ​ሪያ ድረስ ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ። 25የኡ​ዛይ ልጅ ፋልል በማ​ዕ​ዘኑ አን​ጻር ያለ​ው​ንና በዘ​በ​ኞች አደ​ባ​ባይ አጠ​ገብ ከላ​ይ​ኛው የን​ጉሡ ቤት ወጥቶ የቆ​መ​ውን ግንብ ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የፋ​ሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። 26ናታ​ኒ​ምም በዖ​ፌል በው​ኃው በር አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ወጥቶ በቆ​መው ግንብ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው ስፍራ ድረስ ተቀ​መጡ። 27ከእ​ር​ሱም በኋላ ቴቁ​ሐ​ው​ያን ወጥቶ በቆ​መው በታ​ላቁ ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን እስከ ዖፌል ቅጥር ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ።
28ከፈ​ረ​ሶች በር በላይ ካህ​ናቱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ቤ​ታ​ቸው አን​ጻር ሠሩ። 29ከዚ​ያም በኋላ የሄ​ሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የም​ሥ​ራቁ በር ጠባቂ የሴ​ኬ​ንያ ልጅ ሰማያ ሠራ። 30ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ሎ​ምያ ልጅ ሐና​ን​ያና የሴ​ሌፍ ስድ​ስ​ተ​ኛው ልጁ ሐኖን ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ። ከዚ​ያም በኋላ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ። 31ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ራፊ ልጅ#ዕብ. “ከወ​ርቅ አን​ጥ​ረ​ኞች የነ​በረ” ይላል። መል​ክያ እስከ ናታ​ኒ​ምና እስከ ነጋ​ዴ​ዎቹ ቤት ድረስ በሐ​ሜ​ፍ​ቃድ በር አን​ጻር ያለ​ውን እስከ ማዕ​ዘኑ መውጫ ድረስ ሠራ። 32ከማ​ዕ​ዘ​ኑም መውጫ ጀም​ረው እስከ በጎች በር ድረስ ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኞ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ሠሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ