የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 12

12
የሌ​ዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት ስም ዝር​ዝር
1ከሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ከዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና ከኢ​ያሱ ጋር የወ​ጡት ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን እነ​ዚህ ነበሩ፤ ሠራ​ህያ፥ ኤር​ም​ያስ፥ ዔዝራ፤ 2አማ​ርያ፥ መሎክ፥ ሐጡስ፥ 3ሴኬ​ንያ፥ ሬሁም፥ ሜራ​ሞት፤ 4አዶ፥ ጌን​ቶን፥ አብያ፤ 5ሚያ​ሚን፥ መዓ​ድያ፥ ቤልጋ፤ 6ሰማ​ዕያ፥ ዮያ​ሪብ፥ ዮዳ​ኤያ፤#ምዕ. 12 ከቍ. 4 እስከ 6 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 7ሳሎም፥ ዓሞቅ፥ ሔል​ቅ​ያስ፥ ኢዳ​ዕያ፤ እነ​ዚህ በኢ​ያሱ ዘመን የካ​ህ​ና​ቱና የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ።
8ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያሱ፥ በንዊ፥ ቀድ​ም​ኤል፥ ሰራ​ብያ፥ ይሁዳ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር በመ​ዘ​ም​ራን ላይ የተ​ሾመ ማታ​ንያ። 9ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በቅ​ቡ​ቅ​ያና ዑኒ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በአ​ን​ጻ​ራ​ቸው ነበሩ።#ምዕ. 12 ቍ. 9 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 10ኢያ​ሱም ዮአ​ቂ​ምን ወለደ፤ ዮአ​ቂ​ምም ኤሊ​ያ​ሴ​ብን ወለደ፤ ኤሊ​ያ​ሴ​ብም ዮሐ​ዳን ወለደ፤ 11ዮሐ​ዳም ዮና​ታ​ንን ወለደ፤ ዮና​ታ​ንም ይዱ​ዕን ወለደ። 12በዮ​አ​ቂ​ምም ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናቱ ነበሩ፤ ከሠ​ራያ ምራያ፥ ከኤ​ር​ም​ያስ ሐና​ንያ፤ 13ከዕ​ዝራ ሜሱ​ላም፥ ከአ​ማ​ርያ ዮሐ​ናን፤ 14ከማ​ሎክ ዮና​ታን፥ ከሴ​ብ​ንያ ዮሴፍ፤ 15ከሐ​ሪም ዓድና፥ ከመ​ራ​ዮት ሔል​ቃይ፤ 16ከአዶ ዘካ​ር​ያስ፥ ከጌ​ን​ቶን ሜሱ​ላም፤ 17ከአ​ብያ ዝክሪ፥ ከሚ​ያ​ሚ​ንና ከሞ​ዓ​ድያ፥ ፈል​ጣይ፤ 18ከቤ​ልጋ ሳሙኣ፥ ከሰ​ማ​ዕያ ዮና​ታን፤ 19ከዮ​ያ​ሬብ መት​ናይ፥ ከዮ​ዳ​ኤያ ኦዚ፤ 20ከሳ​ላይ ቃላይ፥ ከዓ​ሞቅ ዔቤር፤ 21ከኬ​ል​ቅ​ያስ ሐሳ​ብያ፥ ከኢ​ዳ​ዕያ ናት​ና​ኤል።
22ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በኤ​ል​ያ​ሴ​ብና በዮ​ሐዳ፥ በዮ​ሐ​ና​ንና በያ​ዱዕ ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ተጻፉ፤ ካህ​ና​ቱም በፋ​ር​ሳ​ዊው በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥት ዘመን ተጻፉ። 23የሌዊ ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች እስከ ኤል​ያ​ሴብ ልጅ እስከ ዮሐ​ናን ዘመን ድረስ በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጻፉ። 24የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች አሳ​ብያ፥ ሰር​ብያ፥ ኢያሱ፥ የቀ​ድ​ም​ኤ​ልም ልጆች፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በእ​ነ​ርሱ ፊት ያከ​ብ​ሩና ያመ​ሰ​ግኑ ነበር። 25መታ​ንያ፥ በቅ​ቡ​ቅያ፥ አብ​ድያ፥ ሜሱ​ላም፥ ጤል​ሞን፥ ዓቁብ በበ​ሮች አጠ​ገብ የሚ​ገ​ኙ​ትን ዕቃ ቤቶች ለመ​ጠ​በቅ በረ​ኞች ነበሩ።#ምዕ. 12 ቍ. 25 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የተ​ሟላ አይ​ደ​ለም። 26እነ​ዚ​ህም በኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ በኢ​ያሱ ልጅ በዮ​አ​ቂም በአ​ለ​ቃ​ውም በነ​ህ​ምያ፥ በጸ​ሓ​ፊ​ውም በካ​ህኑ በዕ​ዝራ ዘመን ነበሩ።
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጽር ምረቃ በዓል
27የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር በተ​መ​ረቀ ጊዜ ምረ​ቃ​ውን በደ​ስ​ታና በም​ስ​ጋና፥ በመ​ዝ​ሙ​ርም፥ በጸ​ና​ጽ​ልም፥ በበ​ገ​ናም፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ለማ​ድ​ረግ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ኑን በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ሁሉ ፈለጉ። 28የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም ልጆች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙር​ያና ከሌ​ሎ​ችም#ዕብ. “ከነ​ጦ​ፋቲ” ይላል። መን​ደ​ሮች ተሰ​በ​ሰቡ።
29ከቤት ጌል​ጋ​ልና ከጌባ፥ ከአ​ዝ​ማ​ዊ​ትም#“ከቤት ጌል​ጋ​ልና ከጌባ ከአ​ዝ​ማ​ዊ​ትም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። እርሻ መዘ​ም​ራኑ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙርያ ለራ​ሳ​ቸው መን​ደ​ሮች ሠር​ተ​ዋ​ልና። 30ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ በረ​ኞ​ች​ንም#ዕብ. በሮ​ቹ​ንም” ይላል። ቅጥ​ሩ​ንም አነጹ።
31የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ወደ ቅጥሩ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤#ግሪክ “አወ​ጡ​አ​ቸው ... አቆ​ሙ​አ​ቸው” ይላል። አመ​ስ​ጋ​ኞ​ቹ​ንም በሁ​ለት ታላ​ላቅ ተርታ አቆ​ም​ኋ​ቸው፤ የአ​ን​ዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅ​ጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣ​ያው በር ሄዱ። 32ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ሆሴዕ የይ​ሁ​ዳም አለ​ቆች እኩ​ሌታ፤ 33ዓዛ​ርያ፥ ዕዝራ፥ ሜሱ​ላም፥ 34ይሁዳ፥ ብን​ያም፥ ሰማ​ዕያ፥ ኤር​ም​ያስ፤ 35መለ​ከ​ትም ይዘው ከካ​ህ​ናቱ ልጆች አያ​ሌ​ዎች፥ የአ​ሳ​ፍም ልጅ የዘ​ኩር ልጅ የሚ​ካያ ልጅ የመ​ታ​ንያ ልጅ የሰ​ማ​ዕያ ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ዘካ​ር​ያስ፤ 36ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ዕያ፥ አዘ​ር​ኤል፥ ማዕ​ላይ፥ ጌላ​ላይ፥ መዓይ፥ ናት​ና​ኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው የዳ​ዊ​ትን የዜ​ማ​ውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ በፊ​ታ​ቸው ነበረ። 37በም​ን​ጭም በር አቅ​ን​ተው ሄዱ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ደረጃ፥ በቅ​ጥ​ሩም መውጫ፥ ከዳ​ዊ​ትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሄዱ።
38ሁለ​ተ​ኛ​ውም የአ​መ​ስ​ጋ​ኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕ​ዝ​ቡም እኩ​ሌታ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ነበ​ርን፤ በቅ​ጥ​ሩም ላይ፥ በእ​ቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ 39ከኤ​ፍ​ሬ​ምም በር በላይ፥ በአ​ሮ​ጌው በርና በዓሣ በር፥ በአ​ና​ን​ኤ​ልም ግንብ፥ በሃ​ሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር አጠ​ገብ ቆሙ። 40እን​ዲሁ ሁለቱ የአ​መ​ስ​ጋ​ኞች ክፍ​ሎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቆሙ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እኔና የአ​ለ​ቆች እኩ​ሌታ ነበ​ርን፤ 41ካህ​ና​ቱም ኤል​ያ​ቄም፥ መዕ​ሤያ፥ ሚን​ያ​ሚን፥ ሚካያ፥ ኤል​ዮ​ዔ​ናይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሐና​ንያ መለ​ከት ይዘው፥#ምዕ. 12 ቍ. 38፥ 40 እና 41 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም ፤ ቍ. 42 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የተ​ሟላ አይ​ደ​ለም። 42መዕ​ሤያ፥ ሰማ​ዕያ፥ ኤል​የ​ዜር፥ ኦዚ፥ ዮሐ​ናን፥ ሚል​ክያ፥ ኤላም፥ ኤዝር፥ መዘ​ም​ራ​ኑም በታ​ላቅ ድምፅ ዘመሩ፤ አለ​ቃ​ቸ​ውም ይዝ​ረ​አያ ነበረ። 43እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ደስታ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ደስም አላ​ቸው፤ ሴቶ​ቹና ልጆ​ቹም ደግሞ ደስ አላ​ቸው፤ ደስ​ታ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሩቅ ተሰማ።
44የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ። 45እነ​ር​ሱም መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ሥር​ዐት የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ውን ሥር​ዐት እንደ ዳዊ​ትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎ​ሞን ትእ​ዛዝ ጠበቁ። 46በዳ​ዊ​ትም ዘመን አሳፍ የመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ነበር፤ እነ​ር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዜማ ያመ​ሰ​ግኑ ነበር። 47እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና በነ​ህ​ምያ ዘመን ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑና ለበ​ረ​ኞቹ ፈን​ታ​ቸ​ውን በየ​ዕ​ለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ነገር ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር ለአ​ሮን ልጆች ሰጡ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ