መጽሐፈ ነህምያ 11
11
1የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከዐሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ። 2ሕዝቡም በፈቃዳቸው በኢየሩሳሌም ለመቀመጥ የወደዱትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።
3በኢየሩሳሌምም የተቀመጡት የሀገሩ አለቆች እነዚህ ናችው፤ እስራኤል ግን ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ ናታኒምም፥ የሰሎሞንም አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዳቸው በየርስታቸውና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ተቀመጡ። 4ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ፥ የሰፋጥያስ ልጅ፥ የሰማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ አታያ፤ 5የሴሎ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዮያሪብ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ፥ የኮልሖዜ ልጅ፥ የባሩክ ልጅ መዕሤያ። 6በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ።
7የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የይሳዕያ ልጅ፥ የአትያል ልጅ፥ የመዕሤያ ልጅ፥ የቆላያ ልጅ፥ የፈዳያ ልጅ፥ የዮሐድ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ ሴሎ። 8ከእርሱም በኋላ ጌቤና ሴል ዘጠኝ መቶ ሃያ ስምንት ነበሩ። 9አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበረ፤ የሰኑዋም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ። 10ከካህናቱም የዮያሬብ ልጅ ይዳእያና ያኪን፤ 11የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የማርዮት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ ሣርያ፥ 12የእግዚአብሔርንም የቤቱን ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሃያ ሁለት የመልክያ ልጅ፥ የፋስኩር ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የአማሴ ልጅ፥ የፈላልያ ልጅ፥ የይሮሖም ልጅ ዓዳያ፥ 13ወንድሞቹም የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት መቶ አርባ ሁለት፤ የኢሜር ልጅ፥ የሜሱላሙት ልጅ፥ የአሐዚ ልጅ፥ የኤዝርኤል ልጅ ሐማስያ፥ 14ወንድሞቻቸውም መቶ ሃያ ስምንት ጽኑዓን ኀያላን፤ አለቃቸውም የሐጊዶሌም ልጅ ዘብዲሔል ነበረ።
15ከሌዋውያንም የቡኒ ልጅ፥ የአሳብያ ልጅ፥ የዓዝሪቃም ልጅ፥ የሐሱብ ልጅ ሰማያ፤ 16ከእግዚአብሔርም ቤት በውጭ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሴቤታይና ኢዮዛብድ፤#ምዕ. 11 ቍ. 16 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም ፤ ቍ. 17 ደግሞ በከፊል የለም። 17በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚጀምሩ አለቃው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ ቦቂቦቅያ፥ የኢዶትም ልጅ፥ የጌላል ልጅ፥ የሰሙዓ ልጅ አብድያ። 18በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ።
19በሮቹንም የሚጠብቁ በረኞች፥ ዓቁብና ጤልሞን፥ ወንድሞቻቸውም መቶ ሰባ ሁለት ነበሩ። 20ከእስራኤልም የቀሩት ከካህናትና ከሌዋውያንም እያንዳንዳቸው በየርስታቸው በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ነበሩ። 21ናታኒምም በዖፌል ተቀምጠው ነበር፤ ሲሐና ጊስፋም በናታኒም ላይ ነበሩ።#ምዕ. 11 ቍ. 20 እና 21 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
22በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የመታንያ ልጅ፥ የሐሳብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ። 23በእነርሱም ላይ የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ፤ የመዘምራኑም ሥርዐት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ። 24ከይሁዳም ልጅ ከዛራ ወገን የባስያዘብኤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ።
25ስለ መንደሮቹና ስለ እርሻዎቻቸው ከይሁዳ ልጆች ዐያሌዎች በቂርያትአርባቅና በመንደሮችዋ፥ በዲቦንና በመንደሮችዋም፥ በቃጽብኤልና በመንደሮችዋም፥ 26በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤተፋሌጥ፥ 27በሐጸርሱዓል፥ በቤርሳቤህና በመንደሮችዋ፥ 28በጼቅላቅ፥ በመኮናና በመንደሮችዋ፥ 29በዓይንሪሞን፥ በጼርህ፥ በየርሙት፥#ምዕ. 11 ቍ. 28 እና 29 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 30በዛኖህ፥ በዓዶላም፥ በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። 31የብንያምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማኬማስ፥ በአያል፥ በቤቴልና በመንደሮችዋ፥ 32በዓናቶት፥ በኖብ፥ በሐናንያ፥ 33በሐጾር፥ በራማ፥ በጌትም፤ 34በሐዲድ፥ በሰቡኢም፥ በነብላት፥ 35በሎድ፥ በኣውኖ፥ በጌሐራሲም ተቀመጡ።#ምዕ. 11 ከቍ. 32 እስከ 35 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 36ከሌዋውያንም ተከፍለው በይሁዳና በብንያም ነበሩ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 11: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ