የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 10

10
በጽ​ሑፉ ላይ ያተ​ሙት ሰዎች
1ያተ​ሙ​ትም እነ​ዚህ ናቸው፤ የሐ​ካ​ልያ ልጅ ሐቴ​ር​ሰታ ነህ​ምያ፥ ሴዴ​ቅ​ያስ፤ 2ኦርያ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኤር​ም​ያስ፤ 3ፋሲ​ኩር፥ አማ​ርያ፥ ሚል​ክያ፤ 4ሐጡስ፥ ሰባ​ንያ፥ መሉክ፤ 5ካሪም፥ ሚራ​ሞት፥ አብ​ድያ፤ 6ዳን​ኤል፥ ገን​ቶን፥ ባሩክ፤ 7ሜሱ​ላም፥ አብ​ድያ፥ ሚያ​ሚን፤ 8መዓ​ዝያ፥ ቤል​ጋይ፥ ሰማያ፤ እነ​ዚህ ካህ​ናት ነበሩ።
9ሌዋ​ው​ያ​ኑም የአ​ዛ​ንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኢ​ን​ሐ​ዳድ ልጆች ባንዩ፥ ቀዳ​ም​ኤል፤ 10ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰባ​ንያ፥ ሆዲያ፥ ቆሊጣ፥ ፌል​ዕያ፥ ሐናን፤ 11ሚካ፥ ሬሆብ፥ ሐሳ​ብያ፤ 12ዘኩር፥ ሰራ​ብያ፥ ሰባ​ንያ፤ 13ሆድያ፥ ባኒ፥ ባኑን።
14የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ፋሮስ፥ ፈሐት ሞዓብ፥ ኤላም፥ ዛቱያ፥ ባኒ፤ 15ቡኒ፥ ዓዝ​ጋድ፥ ቤባይ፤ 16አዶ​ን​ያስ፥ በጉ​ዋይ፥ ዓዲን፤ 17አጤር፥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ዓዙር፤ 18አሆ​ዲያ፥ ሐሱም፥ ቤሳይ፤ 19ሐሪፍ፥ ዓና​ቶት፥ ኖባይ፤ 20መግ​ፈ​አስ፥ ሜሱ​ላም፥ ኤዚር፤ 21ሜሴ​ዜ​ቤል፥ ሳዶቅ፥ ያዱአ፤ 22ፈላ​ጥያ፥ ሐናን፥ ዓናያ፤ 23ሆሴዕ፥ ሐና​ንያ፥ አሱብ፥ 24አሎ​ኤስ፥ ፈሊሃ፥ ሶቤቅ፤ 25ሬሁም፥ ሐሰ​ብና፥ መዕ​ሤያ፤ 26አሂያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥፤ 27መሎክ፥ ሔራም፥ ባዕና።
ሕዝቡ የገ​ቡት ቃል ኪዳን
28የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹም፥ መዘ​ም​ራ​ንም፥ ናታ​ኒ​ምም፥ ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ራሳ​ቸ​ውን የለ​ዩና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሚ​ያ​ው​ቁ​ትና የሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንና ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን#ዕብ. “ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸው ተጠጉ” ይላል። አበ​ረ​ታቱ፤ 29በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ። 30ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ን​ንም ለም​ድር አሕ​ዛብ አን​ሰ​ጥም፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለል​ጆ​ቻ​ችን አን​ወ​ስ​ድም፤ 31የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ ሸቀ​ጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገ​በዩ በሰ​ን​በት ቀን ቢያ​መጡ በሰ​ን​በት ወይም በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀን ከእ​ነ​ርሱ አን​ገ​ዛም፤ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዓመት እና​ከ​ብ​ራ​ለን፤ ከሰ​ውም ዕዳ ማስ​ከ​ፈ​ልን እን​ተ​ዋ​ለን።
32ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት ሥራ ሁሉ በየ​ዓ​መቱ የሰ​ቅል ሢሶ እና​መጣ ዘንድ ሥር​ዐት በራ​ሳ​ችን ላይ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። 33ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት፥ ስለ ኅብ​ስተ ገጽም፥ ዘወ​ት​ርም በሰ​ን​በ​ትና በመ​ባቻ ስለ ማቅ​ረብ ስለ እህሉ ቍር​ባ​ንና ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ ስለ በዓ​ላ​ትም፥ ስለ ተቀ​ደ​ሱ​ትም ነገ​ሮች፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስለ​ሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ 34እኛም ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ሕዝ​ቡም፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችን ቤቶች በተ​ወ​ሰነ ጊዜ በየ​ዓ​መቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት አም​ጥ​ተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ይቃ​ጠል ዘንድ ስለ ዕን​ጨት ቍር​ባን ዕጣ ተጣ​ጣ​ልን፤ 35በየ​ዓ​መ​ቱም የመ​ሬ​ታ​ች​ንን እህል ቀዳ​ም​ያት፥ የሁሉ ዓይ​ነት ዛፍ የፍሬ ቀዳ​ም​ያት ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እና​መጣ ዘንድ፥ 36በሕ​ጉም እንደ ተጻፈ የል​ጆ​ቻ​ች​ን​ንና የእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት፥ የበ​ሬ​ዎ​ቻ​ች​ን​ንና የበ​ጎ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት እና​መጣ ዘንድ፥ 37የእ​ህ​ላ​ች​ን​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የዛ​ፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወ​ይ​ኑ​ንና የዘ​ይ​ቱ​ንም ፍሬ ወደ ካህ​ናቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች እና​መጣ ዘንድ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን እርሻ ሁሉ ዐሥ​ራት ይቀ​በ​ላ​ሉና የመ​ሬ​ታ​ች​ንን ዐሥ​ራት ወደ ሌዋ​ው​ያን እና​መጣ ዘንድ ማልን። 38ሌዋ​ው​ያ​ኑም ዐሥ​ራ​ቱን በተ​ቀ​በሉ ጊዜ የአ​ሮን ልጅ ካህኑ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋር ይሁን፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የዐ​ሥ​ራ​ቱን ዐሥ​ራት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ ጓዳ​ዎች ወደ ዕቃ ቤት ያም​ጡት። 39የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የሌዊ ልጆ​ችም የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ​ዎ​ችና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራኑ ወዳ​ሉ​ባ​ቸው ጓዳ​ዎች ያግ​ቡት፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቤት ከቶ አን​ተ​ውም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ