የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 13

13
እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ከአ​ሕ​ዛብ መለ​የ​ታ​ቸው
1በዚ​ያም ቀን የሙ​ሴን መጽ​ሐፍ በሕ​ዝቡ ጆሮ አነ​በቡ፤ አሞ​ና​ው​ያ​ንና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ገቡ የሚል በዚያ አገኙ። 2የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእ​ን​ጀ​ራና በውኃ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምና፥ ይረ​ግ​ማ​ቸ​ውም ዘንድ በለ​ዓ​ምን ገዝ​ተ​ው​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችን ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት መለ​ሰው። 3ሕጉ​ንም በሰሙ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር የተ​ደ​ባ​ለ​ቀ​ውን ሕዝብ ሁሉ ለዩ።
4ከዚ​ህም አስ​ቀ​ድሞ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች ላይ ተሾሞ የነ​በ​ረው ካህኑ ኤል​ያ​ሴብ ከጦ​ብያ ጋር ተወ​ዳ​ጅቶ፥ 5ለሌ​ዋ​ው​ያን፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ንና ለበ​ረ​ኞቹ እንደ ሕጉ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት፥ ለካ​ህ​ና​ቱም የሆ​ነ​ውን ቀዳ​ም​ያ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ያስ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለት ነበር። 6እኔ ግን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሠ​ላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበ​ርና በዚህ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ነ​በ​ር​ሁም። ከጥ​ቂት ዘመ​ንም በኋላ የን​ጉ​ሡን ፈቃድ ለመ​ንሁ፤ 7ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጣሁ፤ ኤል​ያ​ሴ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ለጦ​ቢያ ዕቃ ቤቱን በማ​ዘ​ጋ​ጀት ያደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ነገር አስ​ተ​ዋ​ልሁ። 8እጅ​ግም አስ​ከ​ፋኝ፤ የጦ​ብ​ያ​ንም የቤ​ቱን ዕቃ ሁሉ ከዕቃ ቤት ወደ ውጭ ጣልሁ። 9ዕቃ ቤቶ​ቹ​ንም እን​ዲ​ያ​ነጹ አዘ​ዝሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ​ዎች፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ ዕጣ​ኑ​ንም መልሼ በዚያ አገ​ባሁ።
10ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ፈን​ታ​ቸው እን​ዳ​ል​ተ​ሰጠ፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሌዋ​ው​ያ​ንና መዘ​ም​ራን እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ እር​ሻው እንደ ሄደ ተመ​ለ​ከ​ትሁ። 11እኔም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ስለ ምን ተተወ?” ብዬ ከአ​ለ​ቆቹ ጋር ተከ​ራ​ከ​ርሁ። ሰበ​ሰ​ብ​ኋ​ቸ​ውም፤ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም አቆ​ም​ኋ​ቸው። 12ይሁ​ዳም ሁሉ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት ወደ ዕቃ ቤቶች አመጡ። 13በዕቃ ቤቶ​ችም ላይ ካህ​ኑን ሰሌ​ም​ያን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳዶ​ቅን፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ፈዳ​ያን ሾምሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የመ​ታ​ንያ ልጅ የዘ​ኩር ልጅ ሐናን ነበረ፤ እነ​ር​ሱም የታ​መኑ ሆነው ተገኙ፤ ሥራ​ቸ​ውም ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ማከ​ፋ​ፈል ነበረ። 14አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ አስ​በኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ወረ​ታ​ዬን አታ​ጥፋ።
15በዚ​ያም ወራት በይ​ሁዳ በሰ​ን​በት ቀን የወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያን የሚ​ረ​ግ​ጡ​ትን፥ ነዶም የሚ​ከ​ም​ሩ​ትን፥ የወ​ይ​ኑን ጠጅና የወ​ይ​ኑን ዘለላ፤ በለ​ሱ​ንም፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸክም በአ​ህ​ዮች ላይ የሚ​ጭ​ኑ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​ትን አየሁ፤ ገበ​ያም ባደ​ረ​ጉ​በት ቀን አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸው። 16ደግ​ሞም በእ​ር​ስዋ የተ​ቀ​መጡ#ዕብ. “የጢ​ሮስ ሰዎች ነበሩ” ይላል። ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም ዓሣ​ዎ​ችን፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸቀጥ አም​ጥ​ተው በሰ​ን​በት ቀን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለይ​ሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር። 17ከይ​ሁ​ዳም አለ​ቆ​ችና ታላ​ላ​ቆች ጋር#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ነጻ ከሆ​ኑት ከይ​ሁዳ ልጆች ጋር” ይላል። ተከ​ራ​ከ​ር​ሁና እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ክፉ ነገር ምን​ድን ነው? የሰ​ን​በ​ት​ንስ ቀን ታረ​ክ​ሳ​ላ​ች​ሁን? 18አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ደ​ዚህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን? አም​ላ​ካ​ች​ንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእ​ኛና በዚች ከተማ ላይ አም​ጥቶ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እና​ን​ተስ ሰን​በ​ትን በማ​ር​ከ​ሳ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መዓ​ትን ትጨ​ም​ራ​ላ​ችሁ?”
19ከዚህ በኋላ ሰን​በት ከመ​ግ​ባቱ በፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች ድን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ በሆነ ጊዜ በሮ​ችዋ እን​ዲ​ዘጉ፥ ሰን​በ​ትም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ እን​ዳ​ይ​ከ​ፈቱ አዘ​ዝሁ። በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክም እን​ዳ​ይ​ገባ ከብ​ላ​ቴ​ኖች በዐ​ያ​ሌ​ዎቹ በሮ​ች​ዋን አስ​ጠ​በ​ቅሁ። 20ሁሉም አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ አድ​ረው ገበያ አድ​ር​ገው ነበር። 21እኔም አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውና፥ “ከቅ​ጥሩ ውጭ ለምን ታድ​ራ​ላ​ችሁ? እንደ ገና ብታ​ደ​ር​ጉት እጆ​ችን አነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ” አል​ኋ​ቸው። ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ በሰ​ን​በት ቀን እንደ ገና አል​መ​ጡም። 22ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ራሳ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ነጹ፥ መጥ​ተ​ውም በሮ​ቹን እን​ዲ​ጠ​ብቁ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን እን​ዲ​ቀ​ድሱ ነገ​ር​ኋ​ቸው። “አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ደግሞ አስ​በኝ፥ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ራራ​ልኝ” አልሁ።
23ደግ​ሞም በዚያ ወራት የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ሞ​ንን፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም ሴቶች ያገ​ቡ​ትን አይ​ሁድ አየሁ። 24ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም እኩ​ሌ​ቶቹ በአ​ዛ​ጦን ቋንቋ ይና​ገሩ ነበር፤ በሌ​ሎች ሕዝብ ቋንቋ የሚ​ና​ገ​ሩም ነበሩ፤#“በሌ​ሎች ሕዝብ ቋንቋ የሚ​ና​ገሩ ነበሩ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በአ​ይ​ሁ​ድም ቋንቋ መና​ገር አያ​ው​ቁም ነበር። 25እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ። 26የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን በዚህ ነገር ኀጢ​አት አድ​ርጎ የለ​ምን? በብዙ አሕ​ዛ​ብም መካ​ከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ በአ​ም​ላ​ኩም ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አን​ግ​ሦት ነበር፤ እር​ሱ​ንም እንኳ እን​ግ​ዶች ሴቶች አሳ​ቱት። 27እን​ዲሁ እን​ግ​ዲህ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት ስት​ሠሩ፥ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ሴቶች በማ​ግ​ባት አም​ላ​ካ​ች​ንን ስት​በ​ድሉ አን​ስ​ማ​ባ​ችሁ።”
28ከዋ​ነ​ኛ​ውም ካህን ከኤ​ል​ያ​ሴብ ልጅ ከዮ​ዳሔ ልጆች አንዱ ለሐ​ሮ​ና​ዊው ለሰ​ን​ባ​ላጥ አማች ነበረ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አባ​ረ​ር​ሁት። 29“አም​ላኬ ሆይ፥ ክህ​ነ​ትን የክ​ህ​ነ​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም ቃል ኪዳን ስላ​ፈ​ረሱ አስ​ባ​ቸው።”
30ከእ​ን​ግዳ ነገ​ርም ሁሉ አነ​ጻ​ኋ​ቸው፤ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው፥ 31በየ​ጊ​ዜ​ውም ዕን​ጨት ለሚ​ሸ​ከሙ ሰዎች ቍር​ባን፥ ለበ​ኵ​ራ​ቱም ሥር​ዐት አደ​ረ​ግሁ። “አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በመ​ል​ካም አስ​በኝ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ