መጽሐፈ ነህምያ 12
12
የሌዋውያንና ካህናት ስም ዝርዝር
1ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ ሠራህያ፥ ኤርምያስ፥ ዔዝራ፤ 2አማርያ፥ መሎክ፥ ሐጡስ፥ 3ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜራሞት፤ 4አዶ፥ ጌንቶን፥ አብያ፤ 5ሚያሚን፥ መዓድያ፥ ቤልጋ፤ 6ሰማዕያ፥ ዮያሪብ፥ ዮዳኤያ፤#ምዕ. 12 ከቍ. 4 እስከ 6 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 7ሳሎም፥ ዓሞቅ፥ ሔልቅያስ፥ ኢዳዕያ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።
8ሌዋውያኑም ኢያሱ፥ በንዊ፥ ቀድምኤል፥ ሰራብያ፥ ይሁዳ፥ ከወንድሞቹም ጋር በመዘምራን ላይ የተሾመ ማታንያ። 9ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ።#ምዕ. 12 ቍ. 9 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 10ኢያሱም ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂምም ኤሊያሴብን ወለደ፤ ኤሊያሴብም ዮሐዳን ወለደ፤ 11ዮሐዳም ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ይዱዕን ወለደ። 12በዮአቂምም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ወንድሞቹ ካህናቱ ነበሩ፤ ከሠራያ ምራያ፥ ከኤርምያስ ሐናንያ፤ 13ከዕዝራ ሜሱላም፥ ከአማርያ ዮሐናን፤ 14ከማሎክ ዮናታን፥ ከሴብንያ ዮሴፍ፤ 15ከሐሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፤ 16ከአዶ ዘካርያስ፥ ከጌንቶን ሜሱላም፤ 17ከአብያ ዝክሪ፥ ከሚያሚንና ከሞዓድያ፥ ፈልጣይ፤ 18ከቤልጋ ሳሙኣ፥ ከሰማዕያ ዮናታን፤ 19ከዮያሬብ መትናይ፥ ከዮዳኤያ ኦዚ፤ 20ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፤ 21ከኬልቅያስ ሐሳብያ፥ ከኢዳዕያ ናትናኤል።
22ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮሐዳ፥ በዮሐናንና በያዱዕ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ። 23የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ። 24የሌዋውያኑም አለቆች አሳብያ፥ ሰርብያ፥ ኢያሱ፥ የቀድምኤልም ልጆች፥ ወንድሞቻቸውም እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በእነርሱ ፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር። 25መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድያ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ።#ምዕ. 12 ቍ. 25 በግሪክ ሰባ. ሊ. የተሟላ አይደለም። 26እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ፥ በጸሓፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።
የኢየሩሳሌም ቅጽር ምረቃ በዓል
27የኢየሩሳሌምም ቅጥር በተመረቀ ጊዜ ምረቃውን በደስታና በምስጋና፥ በመዝሙርም፥ በጸናጽልም፥ በበገናም፥ በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ። 28የመዘምራኑም ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙርያና ከሌሎችም#ዕብ. “ከነጦፋቲ” ይላል። መንደሮች ተሰበሰቡ።
29ከቤት ጌልጋልና ከጌባ፥ ከአዝማዊትም#“ከቤት ጌልጋልና ከጌባ ከአዝማዊትም” የሚለው በግሪኩ የለም። እርሻ መዘምራኑ በኢየሩሳሌም ዙርያ ለራሳቸው መንደሮች ሠርተዋልና። 30ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡንም፥ በረኞችንም#ዕብ. በሮቹንም” ይላል። ቅጥሩንም አነጹ።
31የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ አወጣኋቸው፤#ግሪክ “አወጡአቸው ... አቆሙአቸው” ይላል። አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፤ የአንዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄዱ። 32ከእነርሱም በኋላ ሆሴዕ የይሁዳም አለቆች እኩሌታ፤ 33ዓዛርያ፥ ዕዝራ፥ ሜሱላም፥ 34ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሰማዕያ፥ ኤርምያስ፤ 35መለከትም ይዘው ከካህናቱ ልጆች አያሌዎች፥ የአሳፍም ልጅ የዘኩር ልጅ የሚካያ ልጅ የመታንያ ልጅ የሰማዕያ ልጅ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፤ 36ወንድሞቹም ሰማዕያ፥ አዘርኤል፥ ማዕላይ፥ ጌላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሓፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ። 37በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ።
38ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኩሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ 39ከኤፍሬምም በር በላይ፥ በአሮጌው በርና በዓሣ በር፥ በአናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ። 40እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ክፍሎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፤ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኩሌታ ነበርን፤ 41ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥ ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥#ምዕ. 12 ቍ. 38፥ 40 እና 41 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም ፤ ቍ. 42 በግሪክ ሰባ. ሊ. የተሟላ አይደለም። 42መዕሤያ፥ ሰማዕያ፥ ኤልየዜር፥ ኦዚ፥ ዮሐናን፥ ሚልክያ፥ ኤላም፥ ኤዝር፥ መዘምራኑም በታላቅ ድምፅ ዘመሩ፤ አለቃቸውም ይዝረአያ ነበረ። 43እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ ደስታቸውም በኢየሩሳሌም ከሩቅ ተሰማ።
44የይሁዳም ሕዝብ በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለቀዳምያት፥ ለዐሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎችን ሾሙ። 45እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዐት የመንጻታቸውን ሥርዐት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ። 46በዳዊትም ዘመን አሳፍ የመዘምራን አለቃ ነበር፤ እነርሱም እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር። 47እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፤ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 12: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ