የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 4:14-30

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 4:14-30 አማ2000

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል ተመ​ልሶ ወደ ገሊላ ሄደ፤ ዝና​ውም በሀ​ገሩ ሁሉ ተሰማ። በየ​ም​ኵ​ራ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር፤ ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ያደ​ንቁ ነበር፤ ሁሉም ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር። ወደ አደ​ገ​በት ወደ ናዝ​ሬ​ትም ሄደ፤ በሰ​ን​በት ቀንም እን​ዳ​ስ​ለ​መደ ወደ ምኵ​ራብ ገባ፤ ሊያ​ነ​ብም ተነሣ። የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስ​ንም መጽ​ሐፍ ሰጡት፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም በገ​ለጠ ጊዜ እን​ዲህ የሚል የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ስፍራ አገኘ። “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዓመት እሰ​ብክ ዘንድ ላከኝ።” መጽ​ሐ​ፉ​ንም አጥፎ ለተ​ላ​ላ​ኪው ሰጠ​ውና ተቀ​መጠ፤ በም​ኲ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ዐይ​ና​ቸ​ውን አት​ኲ​ረው ተመ​ለ​ከ​ቱት። እር​ሱም፥ “የዚህ የመ​ጽ​ሐፍ ነገር ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ ደረሰ፤ ተፈ​ጸ​መም” ይላ​ቸው ጀመር። ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር። እር​ሱም፥ “በውኑ ባለ መድ​ኀ​ኒት ራስ​ህን አድን፤ በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ሁሉ በዚ​ህም በሀ​ገ​ርህ ደግሞ አድ​ርግ ብላ​ችሁ ይህ​ችን ምሳሌ ትመ​ስ​ሉ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነቢይ በሀ​ገሩ አይ​ከ​ብ​ርም። እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ል​ያስ ዘመን በም​ድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በተ​ዘ​ጋ​በት ጊዜ ብዙ መበ​ለ​ቶች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ። ኤል​ያስ የሲ​ዶና ክፍል በም​ት​ሆን በስ​ራ​ጵታ ወደ​ም​ት​ኖር ወደ አን​ዲት መበ​ለት ሴት እንጂ ከእ​ነ​ዚህ ወደ አን​ዲቱ እን​ኳን አል​ተ​ላ​ከም። በነ​ቢዩ በኤ​ል​ሳዕ ዘመ​ንም ብዙ ለም​ጻ​ሞች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶ​ር​ያ​ዊው ከን​ዕ​ማን በቀር ከእ​ነ​ዚያ አንድ እን​ኳን አል​ነ​ጻም።” በም​ኵ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ይህን ሰም​ተው ተቈጡ። ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥ​ተው ከከ​ተማ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ ገፍ​ተ​ውም ይጥ​ሉት ዘንድ ከተ​ማ​ቸው ተሠ​ር​ታ​ባት ወደ ነበ​ረች ተራራ ጫፍ ወሰ​ዱት። እርሱ ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አልፎ ሄደ።