የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 2:13-16

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 2:13-16 አማ2000

ድን​ገ​ትም ከዚያ መል​አክ ጋር ብዙ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ መጡ። “ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር። ከዚ​ህም በኋላ መላ​እ​ክት ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በዐ​ረጉ ጊዜ እነ​ዚያ እረ​ኞች ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “እስከ ቤተ ልሔም እን​ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የገ​ለ​ጠ​ል​ንን ይህን ነገር እን​ወቅ” አሉ። ፈጥ​ነ​ውም ሄዱ፤ ማር​ያ​ም​ንና ዮሴ​ፍን አገ​ኙ​አ​ቸው፤ ሕፃ​ኑ​ንም በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ አገ​ኙት።