የሉ​ቃስ ወን​ጌል 13:31-35

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 13:31-35 አማ2000

በዚ​ያ​ችም ቀን ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን ሰዎች መጥ​ተው፥ “ከዚህ ውጣና ሂድ፤ ሄሮ​ድስ ሊገ​ድ​ልህ ይሻ​ልና” አሉት። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱና ያችን ቀበሮ እን​ዲህ በሉ​አት፤ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋ​ን​ን​ትን አወ​ጣ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ት​ንም አድ​ላ​ለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን እፈ​ጽ​ማ​ለሁ። ዛሬና ነገስ አለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ግን እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነቢይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንጂ በውጭ ሊሞት አይ​ገ​ባ​ው​ምና። “ነቢ​ያ​ትን የም​ት​ገ​ድ​ሊ​ያ​ቸው፥ ወደ አንቺ የተ​ላ​ኩ​ትን ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም የም​ት​ደ​በ​ድ​ቢ​ያ​ቸው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዶሮ ጫጩ​ቶ​ች​ዋን ከክ​ን​ፍዋ በታች እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ ልጆ​ች​ሽን ልሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ምን ያህል ወደ​ድሁ? ነገር ግን እንቢ አላ​ችሁ። እነሆ፥ ቤታ​ችሁ ምድረ በዳ ሆኖ ይቀ​ር​ላ​ች​ኋል፤ ከዛሬ ወዲያ ‘በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው’ እስ​ክ​ትሉ ድረስ እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።”